እንዲህም በሉ፦ እነሆ አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን ነው። በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ምናልባት ይራራልኛል፤ ፊቱንም አያለሁ ብሎአልና።”
ኢሳይያስ 36:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስንም አትስሙ፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ በሕይወት ልትኖሩ ብትወድዱ ሁላችሁ ወደ እኔ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ትጠጣላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቅያስን አትስሙ። የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፤ ‘ከእኔ ጋራ ተስማሙ፤ ወደ እኔም ውጡ። ከዚያም እያንዳንዳችሁ ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቅያስን አትስሙ፤’ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ‘ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ኑ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፥ ከጉድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ! የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፦ ወደ እኔ ኑና ከእኔ ጋር ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላ የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጒድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቅያስንም አትስሙ፥ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ውጡ፥ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፥ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፥ |
እንዲህም በሉ፦ እነሆ አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን ነው። በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ምናልባት ይራራልኛል፤ ፊቱንም አያለሁ ብሎአልና።”
ከወደድኸኝስ ይህችን ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል፤ እግዚአብሔር ራርቶልኛልና፥ ለእኔም ብዙ አለኝና።” እስኪቀበለውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀበለውም።
ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮች አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ጠበቀው።
በሰሎሞንም ዘመን ሁሉ ይሁዳና እስራኤል ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ እያንዳንዳቸው ከወይኑና ከበለሱ በታች ተዘልለው ይቀመጡ ነበር።
ሕዝቅያስንም አትስሙ፤ የአሶር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ጋር ታረቁ፤ ወደ እኔም ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፤ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፤
እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ ኤልሳዕ ተመለሰ፤ ወደ እርሱም ደርሶ በፊቱ ቆመና፥ “እነሆ፥ በእስራኤል ነው እንጂ በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ ዐወቅሁ፤ አሁንም ከአገልጋይህ በረከት ተቀበል” አለው።
ይህም መጥቼ ምድራችሁን ወደምትመስለው ምድር፥ እህልና የወይን ጠጅ፥ እንጀራና ወይን ወዳለባት ምድር እስካፈልሳችሁ ድረስ ነው።
ስለዚህም አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው በቅድሚያ የተናገራችኋትን በረከታችሁን እንዲያዘጋጁ ወንድሞችን ማለድሁ፤ እንደዚህም የተዘጋጀ ይሁን፤ በረከትን እንደምታገኙበት እንጂ በንጥቂያ እንደ ተወሰደባችሁ አይሁን።
የኢያቢስም ሰዎች፥ “ወደ እስራኤል ሀገር ሁሉ መልእክተኞችን እንድንልክ ሰባት ቀን ቈይልን፤ ከዚያም በኋላ የሚያድነን ባይኖር ወደ አንተ እንመጣለን” አሉት።