ኢሳይያስ 34:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆችዋ ያልቃሉ፤ ነገሥታቷና መሳፍንቷ ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኳንንቷም መንግሥት ተብለው ለመጠራት የሚያስችላቸው ነገር አይኖራቸውም፤ አለቆቿም በሙሉ ጥርግ ብለው ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሳፍንቶችዋን ወደ መንግሥት ይጠራሉ፥ ነገር ግን ማንም አይገኝባትም፤ አለቆችዋም ሁሉ ምናምቴዎች ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገሪቱንም የሚያስተዳድር ንጉሥ አይገኝም፤ መሪዎችም ሁሉ ይወገዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሳፍንቶችዋን ወደ መንግሥት ይጠራሉ፥ ነገር ግን ማንም አይገኝባትም፥ አለቆችዋም ሁሉ ምናምኖች ይሆናሉ። |
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን አለቆች ሁሉ ማርኮ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባፈለሳቸው ጊዜ፥
የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች በዐይኑ ፊት በዴብላታ ገደላቸው፤ የባቢሎንም ንጉሥ የይሁዳን ታላላቆች ሁሉ ገደለ።
ትንቢት ብናገር፥ የተሰውረውን ሁሉ፥ ጥበብንም ሁሉ ባውቅ፥ ተራራ እስከ ማፍለስ የሚያደርስ ፍጹም እምነትም ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
ለጣዖታት የተሠዋውን ስለመብላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደሆነ፥ ከአንድ እግዚአብሔርም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
እነሆ እናንተ ስላገበራችሁኝ በመመካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእኔማ በእናንተ ዘንድ ልከብርና እናንተም ምስክሮች ልትሆኑኝ ይገባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢምንት ብሆንም ዋናዎቹ ሐዋርያት ሁሉ ከሠሩት ሥራ ያጐደልሁባችሁ የለምና።