የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ የጻድቃኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
ኢሳይያስ 33:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሩቅ ያሉ የሠራሁትን ይሰማሉ፤ በቅርብም ያሉ ኀይሌን ያውቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በሩቅ ያላችሁ ያደረግሁትን ስሙ፤ እናንተ በቅርብ ያላችሁ ኀይሌን ዕወቁ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በሩቅ ያላችሁ የሠራሁትን ስሙ፤ እናንተም በቅርብ ያላችሁ ኃይሌን እውቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በሩቅ ያላችሁ የሠራሁትን ስሙ፤ እናንተም በቅርብ ያላችሁ ኀያልነቴን አረጋግጡ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በሩቅ ያላችሁ የሠራሁትን ስሙ፥ እናንተም በቅርብ ያላችሁ ኃይሌን እውቁ። |
የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ የጻድቃኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
ደሴቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተም አሕዛብ፥ አድምጡ፤ ከረዥም ዘመን በኋላ እንዲህ ይሆናል ይላል እግዚአብሔር፤ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠርቶአል፤
እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፤ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።
እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እመታህማለሁ፤ ራስህንም ከአንተ እቈርጠዋለሁ፤ ሬሳህንና የፍልስጥኤማውያንንም ሠራዊት ሬሶች ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ዛሬ እሰጣለሁ። ምድር ሁሉ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር እንዳለ ያውቃሉ፤