ኢሳይያስ 28:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉን ለማን ተናገርን? ወሬን ለማን አወራን? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እንዲህ ይላሉ፤ “የሚያስተምረው ማንን ነው? መልእክቱን የሚያብራራውስ ለማን ነው? ወተት ለተዉት ሕፃናት? ወይስ ጡት ለጣሉት? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ማንን ለማስተማር ይፈልጋል? መልእክቱንስ የሚገልጠው ለማነው? የእርሱ ትምህርት የሚጠቅመው ጡት ለጣሉ ሕፃናት ብቻ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን? |
ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፥ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን” ይላሉ።
እግዚአብሔርም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ይሰጥሃል። የሚያሳስቱህም እንግዲህ ወደ አንተ አይቀርቡም፤ ዐይኖችህ ግን የሚያሳስቱህን ያያሉ፤
ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እንዲህ ይላል፥ “እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ የምትሄድባትንም መንገድ እንዴት እንደምታገኝ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።
የምናገረውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የጥበብ ምላስን ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፤ ለመስማትም ጆሮን ሰጥቶኛል።
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሂድና ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ቃሌን ትሰሙ ዘንድ ተግሣጽን አትቀበሉምን? ይላል እግዚአብሔር።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ? ለማንስ አዳኛለሁ? እነሆ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘች ናት፤ ለመስማትም አይችሉም፤ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል፥ ይሰሙት ዘንድ አልፈቀዱምና።
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።
“አቤቱ፥ ምስክርነታችንን ማን ያምነናል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?” ያለው የነቢዩ የኢሳይያስ ቃል ይደርስ ዘንድ።