የእግዚአብሔርንም ታቦት ከቂርያትይዓሪም ያመጡ ዘንድ ዳዊት እስራኤልን ሁሉ ከግብፅ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ኤማት መግቢያ ድረስ ሰበሰበ።
ኢሳይያስ 23:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የገቡ ስደተኞች አሕዛብ በመከር ጊዜ እንደሚለወጥ ዘር ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በታላላቅ ውሆች ላይ፣ ለጢሮስ የሺሖር እህል ይመጣላት ነበር፤ የአባይ መከር ገቢዋ ነበር፤ እርሷም የመንግሥታቱ የንግድ መናኸሪያ ሆነች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጥልቅ ውኆቿ ላይ የሺሖር እህልና የዓባይ ወንዝ መከር ገቢዋ ነበር፤ እርሷም የአሕዛብ የንግድ መናኸሪያ ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግብጽ የሚመረተው እህል በትልቁ ባሕር በኩል መጥቶ ለጢሮስ ትልቅ ገቢ ይሆናል፤ ስለዚህ ጢሮስ የዓለም ገበያ ሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሺሖር ዘርና የአባይ ወንዝ መከር በብዙ ውኆች ላይ ገቢዋ ነበረ፥ እርስዋም የአሕዛብ መነገጃ ነበረች። |
የእግዚአብሔርንም ታቦት ከቂርያትይዓሪም ያመጡ ዘንድ ዳዊት እስራኤልን ሁሉ ከግብፅ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ኤማት መግቢያ ድረስ ሰበሰበ።
በጢሮስ ላይ ይህን የመከረ ማን ነው? እርስዋ ከሁሉ የምትሻልና የምትበልጥ አይደለችምን? ነጋዴዎችዋ የከበሩ የምድር አለቆች ናቸው።
አሁንስ የግዮንን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብፅ መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የወንዞችንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ?
በባሕር ውስጥ ምን ያህል ዋጋ ታገኚ ነበር? በብልጥግናሽ ብዛት ብዙ አሕዛብን አጠገብሽ፤ ከአንቺም ጋር አንድ ከሆኑት ለይተሽ የምድርን ነገሥታት ሁሉ ባለጸጎች አደረግሻቸው።
በጥበብህና በማስተዋልህ ብልጽግናን ለራስህ አግኝተሃልን? ወርቅንና ብርንም በግምጃ ቤትህ ውስጥ ሰብስበሃልን?
ትወርሳት ዘንድ የምትገባባት ምድር፥ በአትክልት ስፍራ እንደሚዘሩ ዘርህን እንደ ዘራህባት፥ በእግርህም እንዳጠጣሃት፥ እንደ ወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም።
በግብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአምስቱ የፍልስጥኤም ግዛቶች ለጋዛ፥ ለአዛጦን፥ ለአስቀሎና፥ ለጌት፥ ለአቃሮን፥ እንዲሁም ለኤዌዎናውያን በተቈጠረችው በከነዓን ግራ በኩል እስካለችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤