ኢሳይያስ 22:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤላምም ሰዎች አፎታቸውን ተሸከሙ፤ በፈረስ የተቀመጡና አርበኞች ሰዎች፥ የአርበኞችም ሠራዊት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤላም የፍላጻ ሰገባ፣ ፈረሷንና ሠረገላዋን አዘጋጀች፤ ቂርም ጋሻዋን አነገበች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤላምም ከሰረገለኞችና ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ አፎቱን ተሸከመ፥ ቂርም ጋሻውን አነገበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዔላም አገር ወታደሮች በሠረገላና በፈረስ ተቀምጠው ቀስትና ፍላጻ አንግበው መጡ፤ የቂር ወታደሮች ጋሻቸውን አዘጋጅተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤላምም ከሰረገለኞችና ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ አፎቱን ተሸከመ፥ ቂርም ጋሻውን ገለጠ። |
የአሦርም ንጉሥ ሰማው፤ የአሦርም ንጉሥ ወደ ደማስቆ ወጣ፤ ያዛትም፤ ሕዝብዋንም ወደ ቂር አፈለሳቸው፤ ረአሶንንም ገደለው።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከባቢሎንና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላሜጤን፥ ከምሥራቅና ከምዕራብ ለቀሩት ለሕዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
ከባድ ራእይ ተነገረኝ፤ ወንጀለኛው ይወነጅላል፤ በደለኛውም ይበድላል። የኤላም ሰዎችና የሜዶን መልእክተኛ በእኔ ላይ ይመጣሉ። ዛሬ ግን እጨነቃለሁ፤ እረጋጋለሁም።
የደማስቆንም ቍልፎች እሰብራለሁ፤ በአዎን ሸለቆ የሚኖሩትንም ሰዎች አጠፋለሁ፤ የካራን ሰዎች ወገኖችንም እቈራርጣለሁ፤ የሶርያ ሕዝብም ወደ ቂር ይማረካሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።
“የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብፅ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከቀጰዶቅያ፥ ሶርያውያንንም ከጕድጓድ ያወጣሁ አይደለምን?