ኢሳይያስ 19:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለግብፃውያን ራስ ወይም ጅራት፥ መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ያለው ሥራ የላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራስም ይሁን ጅራት፣ የዘንባባ ዝንጣፊም ይሁን ደንገል፣ ለግብጽ የሚያደርጉላት አንዳች ነገር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራስ ይሁን ጅራት፥ የዘንባባ ዝንጣፊ ይሁን ደንገል፥ ለግብጽ አንዳች ነገር ሊያደርጉላት አይችሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግብጽ ባለጸጋም ሆነ ድኻ፥ ዝነኛ የሆነ ወይም ታዋቂነት የሌለው ምንም ነገር ማድረግ አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራስ ወይም ጅራት የሰሌን ቅርንጫፍ እንግጫ ቢሆን ሊሰራ የሚችል ሥራ ለግብጽ አይሆንላትም። |
ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥
እኔም በምድርና በተራሮች፥ በእህልና በወይንም፥ በዘይትና ምድርም በምታበቅለው ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶችም ላይ፥ እጅም በሚደክምበት ሁሉ ላይ ድርቅን ጠርቻለሁ።