ኢሳይያስ 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ በኢያዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለቅሳለሁ፤ ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፥ ዛፎችሽ ወድቀዋል፤ የዛፍሽን ፍሬና የወይንሽን መከር እረግጣለሁ፤ ተክሎችሽ ሁሉ ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ስለ ሴባማ የወይን ተክል፣ ኢያዜር እንዳለቀሰች፣ እኔም አለቅሳለሁ፤ ሐሴቦን ሆይ፤ ኤልያሊ ሆይ፤ በእንባዬ አርስሻለሁ! ፍሬ ባፈራሽበት ወቅት የነበረው ሆታ፣ መከርሽም ሲደርስ የነበረው ደስታ ተቋርጧልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ስለ ሴባማ የወይን ግንድ ከኢያዜር ልቅሶ ጋር አለቅሳለሁ፤ ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፥ በዛፍሽ ፍሬና በወይንሽ መከር የጦር ጩኸት ወድቆአልና በእንባዬ አርስሻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ያዕዜር እንደማለቅስ ስለ ሲብማ የወይን ሐረጎችም አለቅሳለሁ፤ ስለ ሐሴቦንና ስለ ኤልዓሌ እንባዬ ይረግፋል፤ ሕዝቡ የሚደሰትበት መከር አልተገኘባቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በኢያዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ የወይን ግንድ አለቅሳለሁ፥ ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፥ በዛፍሽ ፍሬና በወይንሽ መከር የጦር ጩኸት ወድቆአልና በእንባዬ አረካሻለሁ። |
እነሆ እኔም ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እቆም ዘንድ በመሴፋ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይኑንና ፍሬውን፥ ዘይቱንም አከማቹ፤ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ።”
አይሁድም ሁሉ ከተሰደዱበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ፤ ወደ ይሁዳም ሀገር ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ መሴፋ መጡ፤ ወይንንና የበጋን ፍሬ፥ ዘይትንም እጅግ ብዙ አከማቹ።
“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ኀይል ዋይ በል፤ እርስዋንና የብርቱዎቹን አሕዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው።
ወደ እርሻውም ወጡ፤ ወይናቸውንም ለቀሙ፤ ጠመቁትም፤ የደስታም በዓል አደረጉ፤ ወደ አምላካቸውም ቤት ገቡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ አቤሜሌክንም ረገሙት።