በዚያም መቀመጥ በጀመሩ ጊዜ እግዚአብሔርን አይፈሩትም ነበር፤ እግዚአብሔርም አንበሶችን ሰደደባቸው፤ ይገድሉአቸውም ነበር።
ኢሳይያስ 15:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፤ በዲሞን ላይ ዐረባውያንን አመጣለሁና፤ የሞዓብንና የአርያልን ዘር፥ ከኤዶምያስም የተረፉትን ወስጄ እንደ አራዊት በምድር ላይ እሰድዳቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዲሞን ወንዞች በደም ተሞልተዋል፤ በዲሞን ላይ ግን ከዚያ ነገር የበለጠ አመጣለሁ፤ ከሞዓብ በሚሸሹት፣ በምድሪቱም ላይ በሚቀሩት አንበሳ እሰድዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፤ ገና በዲሞን ላይ ሥቃይን እጨምራለሁ፥ ከሞዓባውያንም በሚያመልጡ፥ ከምድርም በሚቀሩ ላይ አንበሳን እሰዳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዲቦን ከተማ የሚገኘው ወንዝ በደም የተሞላ ነው፤ ሆኖም በዲቦን ላይ እግዚአብሔር ከዚያ የባሰ ነገር ያመጣል፤ ከሞአብ ሸሽተው የሚያመልጡትንና እዚያም ከሞት የተረፉትን ሁሉ አንበሳ ልኮ ያጠፋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፥ በዲሞንም ላይ ሥቃይን እጨምራለሁ፥ ከሞዓባውያንም በሚያመልጡ፥ ከምድርም በሚቀሩ ላይ አንበሳን አመጣለሁ። |
በዚያም መቀመጥ በጀመሩ ጊዜ እግዚአብሔርን አይፈሩትም ነበር፤ እግዚአብሔርም አንበሶችን ሰደደባቸው፤ ይገድሉአቸውም ነበር።
ሰይፍን ለመግደል፥ ውሾችንም ለመጐተት፥ የሰማያትንም ወፎች፥ የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ አራቱን ዓይነት ጥፋት አዝዝባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
“እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።”
ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ይሆናል።