ኢሳይያስ 12:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃውንም ከሕይወት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከድነቴ ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመድኀኒቴ ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከደኅንነት ምንጭ ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ። |
በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በወንድሞች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው።
በተራሮች ላይ ወንዞችን፥ በሸለቆችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ መቆሚያ፥ የተጠማችውንም ምድር ለውኃ መፍለቂያ አደርጋለሁ።
የሚራራላቸውም ያጽናናቸዋልና፥ በውኃ ምንጮችም በኩል ይመራቸዋልና አይራቡም፤ አይጠሙም፤ የፀሐይ ትኩሳትም አይጐዳቸውም።
ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን አድርገዋልና፤ የሕይወት ውኃ ምንጭ እኔን ትተውኛል፥ የተነደሉትን ውኃውንም ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጕድጓዶች ለራሳቸው ቈፍረዋል።
ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በሚገባበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል፤ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ፤ የባሕሩም ውኃ ይፈወሳል፤ ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል።
በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”
ሐናም ጸለየች፤ እንዲህም አለች፦ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በአምላኬ በመድኀኒቴ ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህም ደስ ብሎኛል።