አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
ኢሳይያስ 10:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ሕዝብ ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን የቀሩት ይድናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል ሆይ፤ ሕዝብህ በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ቢሆንም፣ ትሩፉ ብቻ ይመለሳል። ጽድቅ የሰፈነበት ጥፋት ታውጇል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤል ሆይ፤ ሕዝብህ እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም፤ የተረፉት ብቻ ይመለሳሉ። ታላቅና ጻድቅ የሆነ ጥፋት ታውጆአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም እንኳ የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ቢሆንም ከእነርሱ መካከል የሚድኑት የተረፉት ብቻ ናቸው፤ ለሕዝቡ ጥፋት ተገቢ የሆነ እውነተኛ ፍርድ ተዘጋጅቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤል ሆይ፥ የሕዝብህ ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይመለሳል። ጽድቅ የተትረፈረፈበትም ጥፋት ተወስኖአል። |
አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከማኅፀንም ጀምሮ የተሸከምኋችሁ፥ ከሕፃንነትም ጀምሮ ያስተማርኋችሁ፥ ስሙኝ።
እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፥ “ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፥ ቤቶችም ሰው አልቦ እስኪሆኑ፥ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ ነው፤”
በእርስዋም ዘንድ ዐሥረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃጠላል፤ ቅጠሎቻቸውም በረገፉ ጊዜ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሁነው ይቀራሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የወይን ፍሬ በዘለላው በተገኘች ጊዜ፦ በረከት በእርስዋ ላይ አለና አታጥፉት እንደሚባለው፥ ሁሉን እንዳላጠፋ ስለ ባሪያዎች እንዲህ አደርጋለሁ።
ከይሁዳ ወንድ ሰውን ሁሉ ያጠፋል፤ ኀያላኑንም ይጨርሳል፤ ሰፈሩም በሰፊው ምድርና በሀገሮቻቸው ሁሉ ይሞላል፤” እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
ከዳተኞች ልጆች ሆይ! እኔ እገዛችኋለሁና ተመለሱ፤ ይላል እግዚአብሔር። አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ፤ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ፤
ከሰይፍም የሚያመልጡ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች ከግብፅ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ፤ ሊቀመጡም ወደ ግብፅ ምድር የገቡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማናችን ቃል እንዲጸና ያውቃሉ።
የእስራኤልም ልጆች ቍጥር እንደማይሰፈርና እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፤ እንዲህም ይሆናል፤ “እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም” ተብሎ በተነገረበት በዚያ ስፍራ የሕያው አምላክ ልጆች ይባላሉ።
በመረጠው ሰው እጅ በዓለም በእውነት የሚፈርድባትን ቀን ወስኖአልና፤ እርሱን ከሙታን ለይቶ በማስነሣቱም ብዙዎችን ወደ ሃይማኖት መልሶአልና።”
ነገር ግን ልቡናህን እንደ ማጽናትህ፥ ንስሓም እንደ አለመግባትህ መጠን የእግዚአብሔር እውነተና ፍርድ በሚገለጥበት ቀን መቅሠፍትን ለራስህ ታከማቻለህ።
በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው።