እኔና አባቶች በምድር አሕዛብ ሁሉ ያደረግነውን አላወቃችሁምን? የምድርስ ሁሉ አሕዛብ አማልክት ሀገራቸውን ከእጄ ያድኑ ዘንድ በውኑ ተቻላቸውን?
ኢሳይያስ 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ። በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፤ እንደ ተተወ እንቍላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው እጁን ወደ ወፍ ጐጆ እንደሚሰድድ፣ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቍላል እንደሚሰበስቡ፣ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው እጁን ወደ ወፍ ጎጆ እንደሚሰድ፤ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቁላል እንደሚሰበስቡ፤ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዓለም መንግሥታት ሁሉ በእኔ ፊት እንደ ወፍ ጎጆች ነበሩ፤ እንቊላል በቀላሉ እንደሚሰበሰብ ዐይነት ሀብታቸውን ሁሉ ሰብስቤ ወሰድኩ፤ ይህን ባደረግሁ ጊዜ የወፍ ላባ ያኽል እንኳ የተንቀሳቀሰ የለም፤ የወፍ ኩምቢ ያኽል እንኳ ድምፁን ያሰማ የለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጄም የአሕዛብን ኃይል እንደ ወፍ ቤት አገኘች፥ የተተወም እንቍላል እንደሚሰበሰብ እንዲሁ እኔ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፥ ክንፉን የሚያራግብ አፉንም የሚከፍት የሚጮኽም የለም። |
እኔና አባቶች በምድር አሕዛብ ሁሉ ያደረግነውን አላወቃችሁምን? የምድርስ ሁሉ አሕዛብ አማልክት ሀገራቸውን ከእጄ ያድኑ ዘንድ በውኑ ተቻላቸውን?
ከጎረቤቶቻቸው እርሻ ይወስዱ ዘንድ፥ ምድርንም ለብቻቸው ይይዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ፥ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!
በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ድፍረትህና የልብህ ኵራት አነሣሥተውሃል። ቤትህንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።