እግዚአብሔር ግን ራራላቸው፤ ማራቸውም፤ ከአብርሃምና ከይስሐቅ፥ ከያዕቆብም ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን እነርሱን ተመለከተ፤ ሊያጠፋቸውም አልወደደም፤ ፈጽሞም ከፊቱ አልጣላቸውም።
ሆሴዕ 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኔም ዘንድ ተገሠጹ፤ እኔም ክንዳቸውን አጸናሁ፤ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን መከሩብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ አሠለጠንኋቸው፤ አጠነከርኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐደሙብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክንዳቸውን ያስተማርሁና ያጸናሁ እኔ ነበርሁ፤ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን አሴሩብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያሠለጠንኳቸውና ጒልበታቸው አንዲጠነክር ያደረግኹ እኔ ነኝ፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ያሤራሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ክንዳቸውን አስተማርሁና አጸናሁ፥ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን መከሩብኝ። |
እግዚአብሔር ግን ራራላቸው፤ ማራቸውም፤ ከአብርሃምና ከይስሐቅ፥ ከያዕቆብም ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን እነርሱን ተመለከተ፤ ሊያጠፋቸውም አልወደደም፤ ፈጽሞም ከፊቱ አልጣላቸውም።
እግዚአብሔርም ለእስራኤል ታዳጊን ሰጠ፤ ከሶርያውያንም እጅ ዳኑ፤ የእስራኤልም ልጆች እንደ ቀድሞው ጊዜ በድንኳናቸው ተቀመጡ።
አንተ ራስህ በአባታችን በባሪያህ በዳዊት አፍ በመንፈስ ቅዱስ እንዲህ ብለህ የተናገርህ፦ አሕዛብ ለምን ተሰበሰቡ? ሕዝቡስ ለምን ከንቱ ነገርን ተናገሩ?
እግዚአብሔርን ሲያውቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ አላከበሩትም፤ አላመሰገኑትምም፤ ነገር ግን ካዱት፤ በአሳባቸውም ረከሱ፤ ልቡናቸውም ባለማወቅ ጨለመ።
ልብ ሁሉ ይማረክ ዘንድ ኅሊናም ለክርስቶስ ይገዛ ዘንድ በእግዚአብሔር ላይ የሚታበየውንና ከፍ ከፍ የሚለውን እናፈርሳለን።