ሆሴዕ 5:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳ አለቆች ድምበርን እንደሚያፈርሱ ሆነዋል፤ እኔም መዓቴን እንደ ውኃ አፈስስባቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ መሪዎች፣ የወሰን ድንጋዮችን እንደሚነቅሉ ሰዎች ናቸው፤ እንደ ጐርፍ ውሃ፣ ቍጣዬን በላያቸው ላይ አፈስሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ አለቆች ድምበርን እንደሚያፈርሱ ሰዎች ሆነዋል፤ እኔም መዓቴን እንደ ውኃ በእነርሱ ላይ አወርድባቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ መሪዎች የእስራኤልን ድንበር እንደሚያፈርሱ ሰዎች ሆነዋል፤ ስለዚህ እኔ ቊጣዬን እንደ ጐርፍ ውሃ አወርድባቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳ አለቆች ድምበርን እንደሚነቅሉ ሆነዋል፥ እኔም መዓቴን እንደ ውኃ አፈስስባቸዋለሁ። |
አለቆችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፤ ፍርድንም ሊያጣምሙ ይፈልጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱንም አቤቱታ አያዳምጡም።
ብርም በከውር ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጥዋ ትቀልጣላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።”
አሁን በቅርብ መዓቴን አፈስስብሻለሁ፤ ቍጣዬንም እፈጽምብሻለሁ፤ እንደመንገድሽም መጠን እፈርድብሻለሁ፤ ጕስቍልናሽንም ሁሉ አመጣብሻለሁ።
ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ግን ቤቱን ያለ መሠረት በአፈር ላይ የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ጎርፎች ገፉት፤ ወዲያውኑም ወደቀ፤ የዚያም ቤት አወዳደቁ ታላቅ ሆነ።”
“አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር፤ በምትካፈላት ርስትህ አባቶችህ የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል።