በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
ሆሴዕ 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ጊዜ እንዲህ ይሆናል፤ በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ የእስራኤልን ቀስት እሰብራለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ቀን በኢይዝራኤል ሸለቆ፣ የእስራኤልን ቀስት እሰብራለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ የእስራኤልን ቀስት እሰብራለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በኢይዝራኤል ሸለቆ የእስራኤልን ጦር እደመስሳለሁ፤ ስለዚህ የልጅህን ስም ‘ኢይዝራኤል’ ብለህ ጥራው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ የእስራኤልን ቀስት እሰብራለሁ አለው። |
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
ጥፋት በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ተዋጊዎችዋ ተያዙ፤ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እግዚአብሔር ተበቅሎአቸዋልና፥ እግዚአብሔርም ፍዳን ከፍሎአቸዋልና።
ከግራ እጅህም ቀስትህን አስጥልሃለሁ፤ ከቀኝ እጅህም ፍላጾችህን አስረግፍሃለሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ እጥልሃለሁ።
በዚያም ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፥ ከመሬትም ተንቀሳቃሾች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ። ቀስትንና ሰይፍን፥ ጦርንም ከምድሩ እሰብራለሁ፤ ተዘልለሽም ትቀመጫለሽ።
እነርሱም፥ “ተራራማው የኤፍሬም ሀገር አይበቃንም፤ በሸለቆው ውስጥ ለሚኖሩት፥ በቤትሳንና በመንደሮችዋ፥ በኢይዝራኤልም ሸለቆ ለሚኖሩት ከነዓናውያን የተመረጡ ፈረሶችና ሰይፍ አሏቸው” አሉት።