እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛዋ ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል፤ ቀድሶታልም።
ዕብራውያን 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ሰባተኛውም ቀን፥ “እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ” ብሎአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ሰባተኛውም ቀን በአንድ ስፍራ፣ “በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ዐረፈ” ብሏልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ሰባተኛው ቀን በአንድ ስፍራ፥ “እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ፤” ብሎአልና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ሰባተኛው ቀን በአንድ ስፍራ “እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ” ተብሎ ተጽፎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ሰባተኛው ቀን በአንድ ስፍራ፦ እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ ብሎአልና፤ |
እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛዋ ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል፤ ቀድሶታልም።
እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰባተኛውም ቀን ሥራውን ፈጽሞ ስላረፈ፥ በእኔና በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘለዓለም ምልክት ነው።”
ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ እንደምታርፍ ሎሌህና ገረድህ ያርፉ ዘንድ፥ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ በሬህም፥ አህያህም፥ ከብትህም ሁሉ፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ መጻተኛ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ።
ነገር ግን መጽሐፍ እንዲህ ብሎ የመሰከረበት ስፍራ አለ፤ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጐበኘውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?