ዕብራውያን 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ሞትን በመፍራት የተቀጡትን፥ ለባርነት የተገዙትንም ሁሉ ያሳርፋቸው ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በሞት ፍርሀት ባርነት የታሰሩትን ነጻ እንዲያወጣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ታስረው የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ሞትን በመፍራት ምክንያት ዕድሜ ልካቸውን በባርነት ይገዙ የነበሩትን ለመዋጀት ነው። |
ዳግመናም አባ አባት ብለን የምንጮህበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደ ገና ለፍርሀት የባርነት መንፈስን አልተቀበላችሁምና።
ነገር ግን አስቶ በባርነት ከሚገዛው ከዚህ ወጥቶ የእግዚአብሔር ልጆች ወደ አገኙአት የነጻነት ክብር ይገባ ዘንድ ተስፋ አለው።