አቂላ የሚባል አንድ አይሁዳዊም አገኘ፤ የትውልድ ሀገሩም ጳንጦስ ነው፤ እርሱም ከጥቂት ወራት በፊት ከኢጣልያ ተሰዶ መጣ፤ ሚስቱ ጵርስቅላም አብራው ነበረች፤ ቀላውዴዎስ አይሁድ ከሮም እንዲሰደዱ አዝዞ ነበርና ወደ እነርሱ መጣ።
ዕብራውያን 13:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መምህሮቻችሁን ሁሉና ቅዱሳንንም ሁሉ ሰላም በሉ፥ በኢጣልያ ያሉ ሁሉ ሰላም ብለዋችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሪዎቻችሁ ሁሉና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከኢጣሊያ የሆኑትም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመሪዎቻችሁ ሁሉ፥ ለቅዱሳንም ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከኢጣልያ ያሉትም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሪዎቻችሁና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ ከኢጣልያ መጥተው እዚህ ያሉት ክርስቲያኖች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዋኖቻችሁ ሁሉና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከኢጣልያ የሆኑቱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። |
አቂላ የሚባል አንድ አይሁዳዊም አገኘ፤ የትውልድ ሀገሩም ጳንጦስ ነው፤ እርሱም ከጥቂት ወራት በፊት ከኢጣልያ ተሰዶ መጣ፤ ሚስቱ ጵርስቅላም አብራው ነበረች፤ ቀላውዴዎስ አይሁድ ከሮም እንዲሰደዱ አዝዞ ነበርና ወደ እነርሱ መጣ።
ከዚህም በኋላ ፊስጦስ ወደ ቄሣር ወደ ኢጣልያ በመርከብ እንሄድ ዘንድ ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስ ከሌሎች እስረኞች ጋር አብሮ የአውግስጦስ ጭፍራ ለነበረ ዩልዮስ ለሚባል የመቶ አለቃ ተሰጠ።
ሐናንያ ግን መልሶ እንዲህ አለ፥ “አቤቱ፥ ስለዚህ ሰው በኢየሩሳሌም በቅዱሳኖችህ ላይ የሚያደርገውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ጳውሎስና ከወንድማችን ጢሞቴዎስ በቆሮንቶስ ሀገር ላለችው የእግዚአሔር ቤተ ክርስቲያንና በአካይያ ሀገር ላሉ ቅዱሳን ሁሉ፥
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የመንፈስ ቅዱስም አንድነት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። የመቄዶንያ ክፍል በምትሆን በፊልጵስዩስ ተጽፎ በቲቶና በሉቃስ እጅ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የተላከው ሁለተኛዉ መልእክት ተፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ አሜን።
ከኢየሱስ ክርስቶስ ባርያዎች ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ፤ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ጋር በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ቅዱሳን ሁሉ፤
በቈላስይስ ላሉ ቅዱሳንና በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ ወንድሞቻችን፥ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
ለመምህሮቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም፤ ስለ እናንተ በእግዚአብሔር ፊት ምላሽ የሚሰጡ እንደ መሆናቸው፥ ይህን ሳያዝኑ ደስ ብሎአቸው ያደርጉት ዘንድ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉና።
የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን መምህሮቻችሁን ዐስቡ፤ መልካም ጠባያቸውን አይታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው።