ዕብራውያን 11:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓለም የማይገባቸው እነዚህ ናቸው፤ ዱር ለዱርና ተራራ ለተራራ፥ ዋሻ ለዋሻና ፍርኩታ ለፍርኩታም ዞሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓለም ለእነርሱ አልተገባቻቸውምና። በየበረሓውና በየተራራው፣ በየዋሻውና በየጕድጓዱ ተንከራተቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓለም አልተገባቸውምና፥ በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በበረሓ፥ በተራራ፥ በምድር ውስጥ ባሉ ዋሻዎችና ፈፋዎች ዞሩ። በዚህም ዐይነት ዓለም ለእነርሱ ተገቢ ስፍራ ሆና አልተገኘችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። |
ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ፥ መቶውን የእግዚአብሔር ነቢያት ወስጄ፥ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ፥ እንጀራና ውኃ የመገብኋቸውን፥ ይህን ያደረግሁትን ነገር በውኑ አንተ ጌታዬ አልሰማህምን?
ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው ነበር።
እዚያም ወዳለ ዋሻ ገባ፤ በዚያም አደረ፤ እነሆም፥ “ኤልያስ ሆይ! ምን አመጣህ?” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።
ጻድቅ ሰው እንደጠፋ አያችሁ፤ ይህንም በልባችሁ አላሰባችሁም፤ ጻድቃን ሰዎች ይወገዳሉ፤ ጻድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም።
እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን ሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጕድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ የሠራው ጕድጓድ ነበረ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት።
የምድያምም እጅ በእስራኤል ላይ ጠነከረች፤ ከምድያምም ፊት የተነሣ የእስራኤል ልጆች በተራሮችና በገደሎች ላይ ጕድጓድና ዋሻ፥ ምሽግም አበጁ።
ዳዊትም ከዚያ ተነሥቶ አመለጠ፤ ወደ ዔዶላም ዋሻም መጣ፤ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተ ሰብ ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ወደዚያ ወረዱ።
የዚፍ ሰዎችም ከአውክሞዲስ ወደ ሳኦል ወደ ኮረብታው ወጥተው እንዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ቀኝ በጠባቡ በኩል በኤኬላ ኮረብታ ላይ በቄኒ ውስጥ በማሴሬት በእኛ ዘንድ ተሸሽጎ የለምን?
እንግዲህ ዕወቁ፤ ከአያችሁ በኋላ ከእናንተ ጋር እንሄዳለን፤ በዚያችም ምድር ካለ በይሁዳ አእላፍ ሁሉ እፈትሻታለሁ።”
የዚፍ ሰዎችም ከአውክሞዲስ ወደ ኮረብታው ወደ ሳኦል መጥተው፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ ከእኛ ጋር ተሸሽጎ አለ” አሉት።