1 ሳሙኤል 23:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 እንግዲህ ዕወቁ፤ ከአያችሁ በኋላ ከእናንተ ጋር እንሄዳለን፤ በዚያችም ምድር ካለ በይሁዳ አእላፍ ሁሉ እፈትሻታለሁ።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 የሚደበቅባቸውን ቦታዎች ሁሉ ካያችሁ በኋላ ግልጽ መረጃ ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አብሬችሁ እሄዳለሁ፤ ብቻ በዚያ አገር ይገኝ እንጂ በይሁዳ ነገዶች ሁሉ መካከል ከገባበት ጕድጓድ ገብቼ አወጣዋለሁ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ስለዚህ የሚደበቅባቸውን ቦታዎች ሁሉ ካያችሁ በኋላ ግልጽ መረጃ ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አብሬችሁ እሄዳለሁ፤ ብቻ በዚያ አገር ይገኝ እንጂ በይሁዳ ነገዶች ሁሉ መካከል ከገባበት ጉድጓድ ገብቼ አወጣዋለሁ።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 የሚሸሸግባቸውን ስፍራዎች በትክክል አግኙ፤ ያገኛችሁትንም ማስረጃ ወዲያው ይዛችሁልኝ ኑ፤ ከዚያም በኋላ እኔ አብሬአችሁ እሄዳለሁ፤ አሁንም በዚያው ግዛት ውስጥ የሚኖር ከሆነ መላውን የይሁዳ ግዛት ማሰስ ቢያስፈልገኝም እንኳ እርሱን በማደን እይዘዋለሁ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 እርሱ የሚደበቅበትንና የሚሸሸግበትን ስፍራ እዩና እወቁ፥ በእርግጥም ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ከእናንተ ጋር እሄዳለሁ፥ በምድርም ውስጥ ቢሸሸግ በይሁዳ አእላፋት ሁሉ መካከል እፈልገዋለሁ። Ver Capítulo |