እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ በሰዎች በትርና በሰው ልጆች አለንጋ እገሥጸዋለሁ፤
ዕብራውያን 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመላእክትስ ከሆነ ጀምሮ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ” ዳግመኛም፥ “እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጄ ይሆነኛል” ያለው ከቶ ለማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር፣ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤” ወይስ ደግሞ፣ “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመላእክትስ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤” ደግሞም “እኔ አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከቶ ከመላእክት መካከል፥ “አንተ ልጄ ነህ፤ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤” ወይም “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ማንን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመላእክትስ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፥ ደግሞም፦ እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል |
እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ በሰዎች በትርና በሰው ልጆች አለንጋ እገሥጸዋለሁ፤
እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆነኛል፤ ከአንተ አስቀድሞ ከነበሩት እንዳራቅሁ፥ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም።
እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፤ ልጅም ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ የመንግሥቱንም ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጸናለሁ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ልጅ ይሆነኝ ዘንድ መርጬዋለሁና፥ እኔም አባት እሆነዋለሁና ልጅህ ሰሎሞን ቤቴንና አደባባዮቼን ይሠራል።
በሁለተኛው መዝሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’ እንዳለ ኢየሱስን አስነሥቶ ተስፋውን ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአል።
እንዲሁ ክርስቶስም ሊቀ ካህናት ይሆን ዘንድ ራሱን ያከበረ አይደለም፤ ነገር ግን፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለድሁህ” ያለው እርሱ ራሱ ነው።