ሐጌ 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን ግን፥ ዘሩባቤል ሆይ፥ በርታ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ታላቁም ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፥ በርታ፥ እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ፥ በርቱና ሥሩ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አሁን ግን ዘሩባቤል ሆይ፤ በርታ፤ የሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፤ በርታ፤ እናንተም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ በርቱ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘እኔ ከእናንተ ጋራ ነኝና ሥሩ’ ይላል ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን ግን፥ ዘሩባቤል ሆይ፥ በርታ፥ ይላል ጌታ፤ ታላቁ ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፥ በርታ፤ እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ፥ በርቱ፥ ይላል ጌታ፤ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና ሥሩ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን ዘሩባቤል ሆይ! በርታ ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ! በርታ፤ የሀገሪቱ ሕዝብ ሆይ! በርቱ! እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ። እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን ግን፥ ዘሩባቤል ሆይ፥ በርታ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ታላቁም ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፥ በርታ፥ እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ፥ በርቱና ሥሩ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። |
እግዚአብሔር ስለ እስራኤል ሙሴን ያዘዘውን ሥርዐትና ፍርድ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ ብትጠነቀቅ በዚያን ጊዜ ይከናወንልሃል፤ አይዞህ፥ በርታ፤ አትፍራ፤ አትደንግጥም።
ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን፥ “ጠንክር፤ ሰው ሁን፤ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፤ አትደንግጥም፤ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነውን ሥራ ሁሉ እስክትፈጽም ድረስ እርሱ አይተውህም፤ አይጥልህምም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቤት ሕንጻ ምሳሌ፥ የአደባባዩ፥ የቤተ መዛግብቱ፥ የሰገነቱ፥ የውስጡ ቤተ መዛግብት፥ የስርየት ቤቱና፥ የእግዚአብሔር ቤት ምሳሌ።
ከካህናቱም ወገን ልጆች እንግዶቹን ሴቶች ያገቡ ሰዎች ተገኙ፤ ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ልጆችና ከወንድሞቹ ማዓሥያ፥ አልዓዛር፥ ኦሬም፥ ገዳልያ።
በዚያን ጊዜም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፤ እንዲህ ሲል፥ “በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ይህ ለአንተ ምልክት ይሆንሃል፤ ሕዝቡን ከግብፅ በአወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታመልካላችሁ” አለው።
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሱ ይሠራ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቤት ከተመሠረተበት ቀን ጀምሮ ከነቢያት አፍ ይህን ቃል በዚህ ዘመን የሰማችሁ እናንተ ሆይ፥ እጃችሁን አበርቱ።
የነዌንም ልጅ ኢያሱን፥ “የእስራኤልን ልጆች እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ወደ ማለላቸው ምድር ታገባለህና ጽና፤ በርታ፤ እርሱም ከአንተ ጋር ይሆናል” ብሎ አዘዘው።
እነሆ አዝዝሃለሁ፤ በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥም።”
እግዚአብሔርም መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ እግዚአብሔር ከመስፍኑ ጋር ነበረ፤ እግዚአብሔርም በሚዋጉአቸው ሰዎች ፊት ከመከራቸው የተነሣ ይቅር ብሏቸዋልና በመስፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ አዳናቸው።
ከብላቴኖቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መልካም አድርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔሙን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፤ ሰውየውም ጠቢብ፥ ተዋጊም ነው፤ በነገርም ብልህ፥ መልኩም ያማረ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው” አለ።