La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነፍ​ሳ​ችሁ ያለ​ች​በ​ትን ደማ​ች​ሁን ከአ​ራ​ዊት ሁሉ እጅ እሻ​ዋ​ለሁ፤ ከሰ​ውም እጅ፥ ከሰው ወን​ድም እጅ፥ የሰ​ውን ነፍስ እሻ​ለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰውን የገደለ ሁሉ ስለ ሟቹ ደም ተጠያቂ ነው፤ የሟቹን ሰው ደም ከገዳዩ፣ ከእንስሳም ይሁን ከሰው እሻለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፥ ከአራዊት እና ከሰውም ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ በተጠያቂነት ላይ እሻዋለሁ፤ ከእንስሶች ሁሉና ከሰውም ላይ እሻዋለሁ፤ ከሰው ሁሉ የሰውን ሕይወት እሻዋለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፥ ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ ከስውም እጅ ከስው ወንድም እጅ፤ የስውን ነፍስ እሻለሁ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 9:5
26 Referencias Cruzadas  

ሮቤ​ልም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብላ​ቴ​ና​ውን አት​በ​ድሉ ብዬ​አ​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም፤ ስለ​ዚህ እነሆ፥ አሁን ደሙ ይፈ​ላ​ለ​ጋ​ች​ኋል።”


አሁ​ንም እና​ንተ ክፉ​ዎች ሰዎች በቤቱ ውስጥ በአ​ል​ጋው ላይ ጻድ​ቁን ሰው ገደ​ላ​ች​ሁት፤ እነሆ፥ ደሙን ከእ​ጃ​ችሁ እሻ​ለሁ፤ ከም​ድ​ርም አጠ​ፋ​ች​ኋ​ለሁ።”


አን​ተም እንደ ጥበ​ብህ አድ​ርግ፤ ሽበ​ቱ​ንም በሰ​ላም ወደ መቃ​ብር አታ​ው​ር​ደው።


የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ዘር ሁሉ አጠ​ፋች።


እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ኢዮ​አስ አባቱ ኢዮ​አዳ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቸር​ነት አላ​ሰ​በም፤ ልጁ​ንም አዛ​ር​ያ​ስን አስ​ገ​ደ​ለው፤ እር​ሱም ሲሞት፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይየው፤ ይፍ​ረ​ደ​ውም” አለ።


አን​ተ​ንም እማ​ል​ዳ​ለሁ፤ እለ​ም​ን​ህ​ማ​ለሁ፤ ይቅር በለኝ፤ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ ለኀ​ጢ​አ​ቴም አሳ​ል​ፈህ አት​ስ​ጠኝ።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም ክፋ​ቴን አት​መ​ል​ከ​ት​ብኝ፤ በም​ድር ጥል​ቀ​ትም አት​በ​ቀ​ለኝ፤ አቤቱ፥ በን​ስሓ ለሚ​መ​ለሱ ሰዎች፥ አም​ላ​ካ​ቸው አንተ ነህና፥ ቸር​ነ​ትህ በእኔ ላይ ይገ​ለጥ፤ መዳን የማ​ይ​ገ​ባኝ ሲሆን በይ​ቅ​ር​ታህ ብዛት አዳ​ን​ኸኝ።


ደማ​ቸ​ውን የሚ​መ​ራ​መር እርሱ አስ​ቦ​አ​ልና፥ የድ​ሆ​ች​ንም ጩኸት አል​ረ​ሳ​ምና።


“አት​ግ​ደል።


“ሰው ሰውን ቢመታ፥ ቢሞ​ትም፥ የመ​ታው ፈጽሞ ይገ​ደል።


በሕ​ዝ​ብህ መካ​ከል በሸ​ን​ጋ​ይ​ነት አት​ዙር፤ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህም ደም ላይ አት​ቁም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝ።


ሰውን የገ​ደለ ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል።


ሰው​ንም የመ​ታና የገ​ደለ ፈጽሞ ይገ​ደል።


“በብ​ረት መሣ​ሪያ ቢመ​ታው፥ ቢሞ​ትም ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል።


ሰውም በሚ​ሞ​ት​በት በእጁ ባለው ድን​ጋይ ቢመ​ታው፥ የተ​መ​ታ​ውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል።


ሰውም በሚ​ሞ​ት​በት በእጁ ባለው በእ​ን​ጨት መሣ​ሪያ ቢመ​ታው፥ የተ​መ​ታ​ውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳ​ዩም ፈጽሞ ይገ​ደል።


ወይም በጥ​ላቻ እስ​ኪ​ሞት ድረስ በእጁ ቢመ​ታው፥ የመ​ታው ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ባለ ደሙ ወይም ተበ​ቃዩ ባገ​ኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደ​ለው።


ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችኋል።


እር​ሱም በም​ድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖ​ሩ​ባ​ትም ዘንድ ዘመ​ን​ንና ቦታን ወስኖ ሠራ​ላ​ቸው።


“ሰው ግን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ቢጠላ፥ ቢሸ​ም​ቅ​በ​ትም፥ በእ​ር​ሱም ላይ ቢነሣ፥ ቢገ​ድ​ለ​ውም፥ ከእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ቢማ​ጠን፥


የከ​ተ​ማው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ይል​ካሉ፤ ከዚ​ያም ይይ​ዙ​ታል። በባ​ለ​ደ​ሙም እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል፤ ይሞ​ታ​ልም።


እን​ዲሁ ሰባ ወን​ድ​ሞ​ቹን በመ​ግ​ደል አቤ​ሜ​ሌክ በአ​ባቱ ቤት ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ክፋት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መለ​ሰ​በት።