ዘፍጥረት 8:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ርግብ እግርዋን የምታሳርፍበት ስፍራ አላገኘችም፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ተመለሰች፤ ውኃው በምድር ላይ ሁሉ ነበረና፤ እጁን ዘረጋና ተቀበላት፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ውስጥ አገባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ውሃው የምድርን ገጽ ገና እንደ ሸፈነ ስለ ነበር፣ ተመልሳ ኖኅ ወዳለበት መርከብ መጣች፤ እርሱም እጁን ዘርግቶ ተቀበላት፤ ወደ መርከቢቱም አስገባት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለ ነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ ውስጥ አስገባት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለ ነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ ውስጥ አስገባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ርግብ እግርዋን የምታሳርፍበት ስፍራ አለገኘችም፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ተመለሰች ውኃ በምድር ላይ ሁሉ ስለ ነበረ እጁን ዘረጋና ተቀበላት ወደ እርሱም ወደ መርከብ ውስጥ አገባት። |
ከእነርሱም የሚሸሹ ይድናሉ፤ መብረርን እንደሚማር ርግብም በተራራ ላይ ይሆናሉ፤ እኔም በኀጢአታቸው ሁሉ እገድላለሁ።
በእኔም ሰላምን እንድታገኙ ይህን ነገርኋችሁ፤ በዓለም ግን መከራን ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለሙን ድል ነሥቼዋለሁና።”
በእነዚያም አሕዛብ መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ አይሆንም፤ በዚያም እግዚአብሔር ተንቀጥቃጭ ልብ ፥ ፈዛዛ ዐይን፥ ደካማም ነፍስ ያመጣብሃል።