Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 8:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ነገር ግን ውሃው የምድርን ገጽ ገና እንደ ሸፈነ ስለ ነበር፣ ተመልሳ ኖኅ ወዳለበት መርከብ መጣች፤ እርሱም እጁን ዘርግቶ ተቀበላት፤ ወደ መርከቢቱም አስገባት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለ ነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ ውስጥ አስገባት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለ ነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ ውስጥ አስገባት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ነገር ግን ርግብ እግ​ር​ዋን የም​ታ​ሳ​ር​ፍ​በት ስፍራ አላ​ገ​ኘ​ችም፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ተመ​ለ​ሰች፤ ውኃው በም​ድር ላይ ሁሉ ነበ​ረና፤ እጁን ዘረ​ጋና ተቀ​በ​ላት፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ውስጥ አገ​ባት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ነገር ግን ርግብ እግርዋን የምታሳርፍበት ስፍራ አለገኘችም፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ተመለሰች ውኃ በምድር ላይ ሁሉ ስለ ነበረ እጁን ዘረጋና ተቀበላት ወደ እርሱም ወደ መርከብ ውስጥ አገባት።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 8:9
8 Referencias Cruzadas  

ሰባት ቀን ከቈየ በኋላ ኖኅ ርግቧን እንደ ገና ላካት።


ከዚያም በኋላ፣ ኖኅ ውሃው ከምድር ገጽ ጐድሎ እንደ ሆነ ለማወቅ ርግብን ላከ፤


ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና።


“ርግቦች ወደ ጐጇቸው እንደሚበርሩ፣ እንደ ደመና የሚጓዙ እነዚህ እነማን ናቸው?


ተርፈው ያመለጡት ሁሉ በሸለቆ እንደሚኖሩ ርግቦች ስለ ኀጢአታቸው እያለቀሱ በተራራ ላይ ይሆናሉ።


“እናንተ ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ።


“በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህን ነግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”


በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ ቦታ አይኖርም። እዚያም እግዚአብሔር የሚጨነቅ አእምሮ፣ በናፍቆት የሚደክም ዐይንና ተስፋ የሚቈርጥ ልብ ይሰጥሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos