ዘፍጥረት 7:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኖኅ በተወለደ በስድስት መቶኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ቀን፣ በዚያ ቀን የታላቁ ጥልቅ ምንጮች በሙሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኖኅ ስድስት መቶ ዓመት በሆነው፥ በሁለተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ፥ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ጥልቅ መፍለቂያዎች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፥ የሰማያትም መስኮቶች ተከፈቱ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኖኅ 600 ዓመት በሆነው ጊዜ፥ በሁለተኛው ወር በዐሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ውሃ ምንጮች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፤ በሰማይ ያሉት የውሃ መስኮቶች ሁሉ ተከፈቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ስባተኛው ዕለት በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ |
እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
ያም ሎሌ ለኤልሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግዚአብሔር በሰማይ የእህል ሿሿቴ ቢያወርድ ይህ ነገር ይሆናልን?” ብሎ ነበር፤ ኤልሳዕም፥ “እነሆ፥ በዐይኖችህ ታየዋለህ፥ ከዚያም አትቀምስም” ብሎት ነበር።
ንጉሡም በእጁ ተደግፎት የሚቆም የነበረ ያ ብላቴና ለኤልሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግዚአብሔር በሰማይ የእህል ሿሿቴ ቢያደርግ ይህ ነገር ይሆናልን?” አለው። ኤልሳዕም፥ “እነሆ፥ በዐይኖችህ ታየዋለህ፤ ከዚያ ግን አትቀምስም” አለ።
በአፈር ምክንያት እንደሚከፈል ወንዝ የጽድቅን መንገድ የረሱ በኀጢአታቸው ይደክማሉ። ከሰዎችም መካከል ይለያሉ።
የሰማይ መስኮቶችም ተከፍተዋልና፥ የምድርም መሠረት ተናውጣለችና ከፍርሀት ድምፅ የሸሸ በገደል ይወድቃል፤ ከገደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል።
በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢትረፈረፍና ቢጮኽ ከእርሱ አያልፍም።
ድምፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፤ ከምድርም ዳር ደመናትን ያወጣል፤ ለዝናብም ጊዜ መብረቅን ያደርጋል፤ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰው እንደሌለባቸው ከተሞች ባድማ ከተማ ባደረግሁሽ ጊዜ፥ ቀላዩንም ባወጣሁብሽ ጊዜ፥ ብዙ ውኆችም በከደኑሽ ጊዜ፥
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።