“ሮቤል እርሱ የበኵር ልጄና ኀይሌ፥ የልጆችም መጀመሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አንገቱንም አደነደነ። ጭንቅ ነገርንም አደረገ።
ዘፍጥረት 49:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንት የያዕቆብ ልጆች ኑ፥ ተሰብሰቡ፤ ስሙም፤ አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ ተሰብሰቡና ስሙ፤ አባታችሁ እስራኤልንም ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንት የያዕቆብ ልጆች ተሰብሰቡ፥ ስሙም፥ አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የያዕቆብ ልጆች፥ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ አባታችሁ እስራኤል የሚነግራችሁንም አድምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንት የያዕቆብ ልጆች ተሰብስቡ፥ ስሙም አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ። |
“ሮቤል እርሱ የበኵር ልጄና ኀይሌ፥ የልጆችም መጀመሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አንገቱንም አደነደነ። ጭንቅ ነገርንም አደረገ።
ሁሉም በአንድነት ተሰብስበው ይሰማሉ፤ ይህን ማን ነገራቸው? አንተን በመውደድ የከለዳውያንን ዘር አስወግድ ዘንድ ፈቃድህን በባቢሎን ላይ አደረግሁ።