ዘፍጥረት 48:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ከአሞራውያን እጅ በሰይፌና በቀስቴ የወሰድሁትን ምርኮ ለአንተ ከወንድሞችህ የተሻለውን እሰጥሃለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ በሰይፌና በቀስቴ ከአሞራውያን እጅ የወሰድኋትን ዐምባ ከወንድሞችህ ድርሻ አብልጬ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ከአሞራውያን በሰይፌና በቀስቴ የወስድሁትን ለአንተ ከወንድሞችህ አንድ እጅ አብልጬ ሰጠሁህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰይፌና በቀስቴ ከአሞራውያን እጅ የወሰድኩትን ለሙን ምድር ሴኬምን፥ ከወንድሞችህ ጋር ከምታገኘው ድርሻ በላይ ለአንተ ብቻ ሰጥቼሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ከአሞራውያን በሰይፌና በቀስቴ የውስድሁትን ለአንተ ከወንድሞችህ አንድ እጅ አብልጬ ሰጠሁህ አለው። |
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ርስት አድርጋችሁ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ምድሪቱን የምትከፍሉበት ድንበር ይህ ነው። ለዮሴፍ ሁለት ዕጣ ይሆናል።
እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ወይራ ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁ፤ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።
ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኀይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው።
የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ያወጡትን የዮሴፍን አፅም ያዕቆብ በሰቂማ ከሚኖሩ ከአሞራውያን በመቶ በጎች በገዛው ለዮሴፍ ድርሻ አድርጎ በሰጠው እርሻ በአንዱ ክፍል በሰቂማ ቀበሩት።
አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ከእስራኤል ፊት አሞሬዎናውያንን አስወገደ፤ አንተም በተራህ ትወርሳለህን?