ብሩም በግብፅ ምድርና በከነዓን ምድር አለቀ፤ የግብፅ ሰዎችም ሁሉ ወደ ዮሴፍ መጡ፤ እንዲህ ሲሉ፥ “በፊትህ እንዳንሞት እህል ስጠን፤ ብሩ አልቆብናልና።”
ዘፍጥረት 47:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም፥ “ከብቶቻችሁን አምጡልኝ፤ ብር ከአለቀባችሁ በከብቶቻችሁ ፈንታ እህል እሰጣችኋለሁ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም፣ “ከብቶቻችሁን አምጡ፤ ገንዘባችሁ ካለቀ በከብቶቻችሁ ለውጥ እህል እሰጣችኋለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም፦ “ከብቶቻችሁን አምጡልኝ፥ ብር ካለቀባችሁ በከብቶቻችሁ ፋንታ እህል እሰጣችኋለሁ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍም “ገንዘባችሁ ካለቀ ከብቶቻችሁን አምጡና በእነርሱ ለውጥ እህል እሰጣችኋለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም፦ ከብቶቻችሁን አምጡልኝ ብር ካለቀባችሁ በከብቶቻችሁ ፋንታ እህል እሰጣችኍለሁ አለ። |
ብሩም በግብፅ ምድርና በከነዓን ምድር አለቀ፤ የግብፅ ሰዎችም ሁሉ ወደ ዮሴፍ መጡ፤ እንዲህ ሲሉ፥ “በፊትህ እንዳንሞት እህል ስጠን፤ ብሩ አልቆብናልና።”
ከብቶቻቸውንም ወደ ዮሴፍ አመጡ፤ ዮሴፍም በፈረሶቻቸው፥ በበጎቻቸውም፥ በላሞቻቸውም፥ በአህዮቻቸውም ፈንታ እህልን ሰጣቸው፤ በዚያች ዓመትም ስለ ከብቶቻቸው ሁሉ ፈንታ እህልን መገባቸው።
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ እውነትን ሁሉ፥ ቅንነትንም ሁሉ፥ ጽድቅንም ሁሉ፥ ንጽሕናንም ሁሉ፥ ፍቅርንና ስምምነትንም ሁሉ፥ በጎነትም ቢሆን፥ ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ አስቡ።