የያዕቆብም ልጆች ከምድረ በዳ መጡ፤ ይህንም በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ደነገጡ፤ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፤ እጅግም ተቈጡ፤ እንዲህ አይደረግምና።
ዘፍጥረት 46:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ወንዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆቹንና የሴቶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስገባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ግብጽም የወረደው፣ ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹንና ሴቶች የልጅ ልጆቹን፣ ማለትም ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብጽ ወሰደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብረው የሄዱትም ወንዶች ልጆቹ፥ ሴቶች ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስገባቸው። |
የያዕቆብም ልጆች ከምድረ በዳ መጡ፤ ይህንም በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ደነገጡ፤ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፤ እጅግም ተቈጡ፤ እንዲህ አይደረግምና።
ከአባታቸው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው፤ ያዕቆብና ልጆቹ፤ የያዕቆብ በኵር ሮቤል።
እንዳያጠፋቸው የቍጣውን መቅሠፍት ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ባጠፋቸው ነበር አለ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕዝቤ አስቀድሞ ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚያም በስደት ኖሩ፤ ከዚያም ወደ አሦር በግድ ተወሰዱ።
በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ አባቴ ከሶርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም በቍጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚያም ታላቅና የበረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።
ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ የያዕቆብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረቱም፤ ግብፃውያንም መከራ አጸኑባቸው።