La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 46:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጓዛ​ቸ​ውን፥ በከ​ነ​ዓን ሀገ​ርም ያገ​ኙ​ትን ጥሪ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይዘው ያዕ​ቆ​ብና ዘሩ ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብጽ ወረዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብና ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብጽ መጡ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከብቶቻቸውንና በከነዓን ያፈሩትን ሀብት ሁሉ ይዘው ወደ ግብጽ ሄዱ፤ በዚህ ዐይነት ያዕቆብ ቤተሰቡን ሁሉ ይዞ ወደ ግብጽ ሄደ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብ ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 46:6
10 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን አለው፥ “ዘርህ ለእ​ነ​ርሱ ባል​ሆ​ነች ምድር ስደ​ተ​ኞች እን​ዲ​ሆኑ በእ​ር​ግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመ​ታ​ትም ባሪ​ያ​ዎች አድ​ር​ገው ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ያሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ዋል፤ ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸ​ዋ​ልም።


ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንና የወ​ን​ዶች ልጆ​ቹን ወን​ዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩ​ንም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስ​ገ​ባ​ቸው።


እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው የቍ​ጣ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ልስ ዘንድ የተ​መ​ረ​ጠው ሙሴ በመ​ቅ​ሠ​ፍት ጊዜ በፊቱ ባይ​ቆም ኖሮ፥ ባጠ​ፋ​ቸው ነበር አለ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕዝቤ አስ​ቀ​ድሞ ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚ​ያም በስ​ደት ኖሩ፤ ከዚ​ያም ወደ አሦር በግድ ተወ​ሰዱ።


አባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በግ​ብ​ፅም እጅግ ዘመን ተቀ​መ​ጥን፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደሉ።


“ያዕ​ቆ​ብም ወደ ግብፅ ወረደ፥ እር​ሱም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሞቱ።


አባ​ቶ​ችህ ሰባ ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወረዱ፤ አሁን ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብዛ​ት​ህን እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አደ​ረገ።


በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ አባቴ ከሶ​ርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚ​ያም በቍ​ጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚ​ያም ታላ​ቅና የበ​ረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።


ለይ​ስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዔሳ​ውን ሰጠ​ሁት፤ ለዔ​ሳ​ውም የሴ​ይ​ርን ተራራ ርስት አድ​ርጌ ሰጠ​ሁት፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረ​ቱም፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም መከራ አጸ​ኑ​ባ​ቸው።


ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብ​ጻ​ው​ያን አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ላከ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ አው​ጥ​ተው በዚህ ቦታ አኖ​ሩ​አ​ቸው።