ዘፍጥረት 46:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ሰረገላውን አዘጋጀ፤ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ኤሮስ ከተማ ወጣ፤ በአየውም ጊዜ አንገቱን አቀፈው፤ ረዥም ጊዜም አለቀሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍ ሠረገላውን አዘጋጅቶ፤ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጌሤም አመራ። ዮሴፍ አባቱ ዘንድ እንደ ደረሰ፣ ዐንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ለረዥም ጊዜ አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ሠረገላውን አዘጋጀ፥ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ጌሤም ወጣ፥ ባየውም ጊዜ በአንገቱ ላይ ወደቀ፥ አቅፎትም ረጅም ጊዜ አለቀሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ አባቱን ለመገናኘት በሠረገላው ተቀምጦ ወደዚያ ሄደ፤ በተገናኙም ጊዜ ዮሴፍ በአባቱ አንገት ላይ ተጠምጥሞ ለብዙ ጊዜ አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ሰረገላውን አዘጋጀ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ጌሤም ወጣ ባየውም ጊዜ በአንገቱ ላይ ወደቀ አቅፎትም ረጅም ጊዜ አለቀሰ። |
የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው፤ ስገዱ እያለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እንዲሄድ አደረገ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው።
አንተም ወንድሞችህን፦ እንዲህ አድርጉ በላቸው፤ ከግብፅ ምድር ለሕፃኖቻችሁ፥ ለሴቶቻችሁም ሰረገሎችን ውሰዱ፤ አባታችሁንም ይዛችሁ ኑ፤
የእስራኤል ልጆችም እንደ አዘዛቸው አደረጉ፤ ዮሴፍም የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን እንደ ነገረው ሰረገሎችንና ለመንገድ ስንቅን ሰጣቸው፤