La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 44:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህ​ንም ከእኔ ለይ​ታ​ችሁ ደግሞ ብት​ወ​ስ​ዱት በመ​ን​ገ​ድም ክፉ ቢያ​ገ​ኘው፥ እር​ጅ​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁን ደግሞ ይህን ልጅ ወስዳችሁ አንዳች ጕዳት ቢደርስበት ሽበቴን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁን ደግሞ ይህን ልጅ ወስዳችሁ አንዳች ጉዳት ቢደርስበት ሽበቴን በመሪር ኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።’

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አሁን ደግሞ ይህንን ወስዳችሁ በእርሱ ላይ አደጋ ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን የምታመጡብኝ ሐዘን ወደ መቃብር ያወርደኛል።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይህንም ከእኔ ለይታችሁ ደግሞ ብትወስዱት ክፋም ቢያገኘው ሽበቴን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 44:29
8 Referencias Cruzadas  

ወን​ዶች ልጆ​ቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ። ኀዘ​ኑ​ንም ያስ​ተ​ዉት ዘንድ አባ​ታ​ቸ​ውን ማለ​ዱት። ኀዘ​ኑ​ንም መተ​ውን እንቢ አለ፥ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃ​ብር እያ​ዘ​ንሁ እወ​ር​ዳ​ለሁ።” አባ​ቱም ስለ እርሱ አለ​ቀሰ።


አባ​ታ​ቸው ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ልጅ አልባ አስ​ቀ​ራ​ች​ሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስም​ዖ​ንም የለም፤ ብን​ያ​ም​ንም ትወ​ስ​ዱ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።”


እር​ሱም አለ፥ “ልጄ ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ወ​ር​ድም፤ ወን​ድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀር​ቶ​አ​ልና፤ በም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ ምና​ል​ባት ክፉ ነገር ቢያ​ገ​ኘው ሽም​ግ​ል​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።”


የዮ​ሴ​ፍን ወን​ድም ብን​ያ​ምን ግን ያዕ​ቆብ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር አል​ሰ​ደ​ደ​ውም፥ “ምና​ል​ባት ክፉ እን​ዳ​ያ​ገ​ኘው” ብሎ​አ​ልና።


አም​ላ​ኬም በዚያ ሰው ፊት ሞገ​ስን ይስ​ጣ​ችሁ፤ ያን ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንና ብን​ያ​ም​ንም ይመ​ል​ስ​ላ​ችሁ፤ እኔም ልጆ​ችን እን​ዳ​ጣሁ አጣሁ።”


ብላ​ቴ​ናው ከእኛ ጋር እን​ደ​ሌለ በአየ ጊዜ ይሞ​ታል፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን የአ​ባ​ታ​ች​ንን እር​ጅና በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር እና​ወ​ር​ዳ​ለን።


በዚ​ያም ቀን ቍጣዬ ይነ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እተ​ዋ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ፊቴ​ንም ከእ​ነ​ርሱ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም መብል ይሆ​ናሉ፤ በዚ​ያም ቀን፦ በእ​ው​ነት አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ና​ልና፥ በእ​ኛም መካ​ከል የለ​ምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገ​ኘን እስ​ኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገ​ርና ጭን​ቀት ይደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋል።