ዘፍጥረት 44:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም ለአገልጋዮችህ፦ ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም እጠብቀዋለሁ አልህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚያም አንተ አገልጋዮችህን፣ ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልኸን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አንተ አገልጋዮችህን፥ ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልኸን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተም ‘አየው ዘንድ ይዛችሁልኝ እንድትመጡ’ አልከን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ለባሪያዎችህ፦ ወደ እኔ አምጡት እኔም አየዋለሁ አልህ። |
ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡ፤ ነገራችሁ የታመነ ይሆናልና፤ ይህ ከአልሆነ ግን ትሞታላችሁ።” እንዲህም አደረጉ።
ዮሴፍም ዐይኑን አንሥቶ የእናቱን ልጅ ወንድሙ ብንያምን አየው፤ እርሱም አለ፥ “ወደ አንተ እናመጣዋለን ብላችሁ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነውን?” እነርሱም፥ “አዎን” አሉት። እንዲህም አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ።”
ዐይኔንም ለበጎነት በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ወደዚህችም ምድር ለመልካም እመልሳቸዋለሁ፤ እሠራቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።
አሁንም እነሆ በእጅህ ካለችው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፤ እኔም በመልካም አይሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ተቀመጥ፤ ተመልከት፥ እነሆ፥ ሀገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ትሄድ ዘንድ መልካም መስሎ በሚታይህና ደስ በሚያሰኝህም ስፍራ ተቀመጥ።”
በጠላቶቻቸውም ፊት ተማርከው ቢሄዱ በዚያ ሰይፍን አዝዛታለሁ፤ እርስዋም ትገድላቸዋለች፤ ዐይኔንም ለመልካም ሳይሆን ለክፋት በእነርሱ ላይ እጥላለሁ።”