አብርሃምም እንደገና ነገሩን ደገመ፤ እንዲህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ሠላሳው አላጠፋትም” አለው።
ዘፍጥረት 44:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እንዲህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ በፊትህ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ፤ እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ፤ አንተ ከፈርዖን ቀጥለህ ነህና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖንን ያህል የተከበርህ ስለ ሆንህ፣ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፥ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖን ያህል የተከበርህ ስለሆንህ፥ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁዳ ወደ ዮሴፍ ቀርቦ እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ አንድ ቃል እንድናገር ፍቀድልኝ፤ ምንም እንኳ የፈርዖንን ያኽል የተከበርክ ብትሆን እባክህ አትቈጣኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ እንዲህም አለ፦ ጌታዬ ሆይ እኔ ባርያን በጌታዬ ጆሮ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ እኔንም ባሪያህን አትቆጣኝ አንተ እንደ ፈርዖን ነህና። |
አብርሃምም እንደገና ነገሩን ደገመ፤ እንዲህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ሠላሳው አላጠፋትም” አለው።
አብርሃምም አለው፥ “አቤቱ እንደገና እናገር ዘንድ ፍቀድልኝ፤ ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ዐሥሩ አላጠፋትም” አለው።
እነሆ፥ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶዎች በዙርያ ከብበው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
ወንድሞቹም፥ “በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ገዢ ትሆነን ይሆን?” አሉት። እንደገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ የበለጠ ጠሉት።
ዮሴፍም አላቸው፥ “ይህን አደርግ ዘንድ አይገባኝም፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው እርሱ አገልጋይ ይሁነኝ እንጂ፤ እናንተ ግን ወደ አባታችሁ በደኅና ሂዱ።”
“እናንተ ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት ነገር እንደ ሞተ እንደ ተቀበረም፥ መቃብሩም እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ እንደ አለ ገልጬ እንድነግራችሁ ትፈቅዱልኛላችሁን?