Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 32:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አሮ​ንም እን​ዲህ አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእኔ ላይ አት​ቈጣ፤ የዚ​ህን ሕዝብ ጠባይ አንተ ታው​ቃ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አሮንም መልሶ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አትቈጣ” ብሎ መለሰለት፤ “ይህ ሕዝብ ሁልጊዜ ለክፋት ያዘነበለ መሆኑን አንተ ታውቃለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 አሮንም እንዲህ አለ፦ “የጌታዬ ቁጣ አይንደድ፤ ይህ ሕዝብ ክፋ እንደሆነ አንተ ታውቃለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አሮንም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታዬ በእኔ ላይ አትቈጣ፤ ይህ ሕዝብ ምን ያኽል የክፋት ዝንባሌ እንዳለው አንተ ታውቃለህ

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አሮንም እንዲህ አለ፦ ጌታዬ ሆይ፥ ቁጣህ አይቃጠል፤ ይህ ሕዝብ ክፋትን እንዲወድድ አንተ ታውቃለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 32:22
17 Referencias Cruzadas  

ይሁ​ዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በፊ​ትህ አን​ዲት ቃልን እን​ድ​ና​ገር እለ​ም​ና​ለሁ፤ እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አት​ቈ​ጣኝ፤ አንተ ከፈ​ር​ዖን ቀጥ​ለህ ነህና።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ልህ፥ የል​ብ​ህ​ንም መሻት ይሰ​ጥ​ሃል።


ሙሴ​ንም አሉት፥ “በግ​ብፅ መቃ​ብር ስላ​ል​ኖረ በም​ድረ በዳ እን​ሞት ዘንድ አወ​ጣ​ኸን? ከግ​ብፅ ታወ​ጣን ዘንድ ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው?


ሕዝ​ቡም፥ “ምን እን​ጠ​ጣ​ለን?” ብለው በሙሴ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


ነገር ግን ሙሴን አል​ሰ​ሙ​ትም፤ አን​ዳ​ንድ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ለነገ አስ​ቀሩ፤ እር​ሱም ተላ፤ ሸተ​ተም፤ ሙሴም ተቈ​ጣ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ትእ​ዛ​ዞ​ች​ንና ሕጎ​ችን ለመ​ስ​ማት እስከ መቼ እንቢ ትላ​ላ​ችሁ?


ሕዝ​ቡም ሙሴ ከተ​ራ​ራው ሳይ​ወ​ርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰ​ብ​ስ​በው፥ “ይህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አና​ው​ቅ​ምና ተነ​ሥ​ተህ በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክት ሥራ​ልን” አሉት።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “ይህን ታላቅ ኀጢ​አት ታመ​ጣ​በት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደ​ረ​ገህ?” አለው።


ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ከዐይናቸው እንቅልፋቸው ይወገዳል አይተኙምም።


እኔ ዐመ​ፃ​ች​ሁ​ንና የአ​ን​ገ​ታ​ች​ሁን ድን​ዳኔ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ እኔም ዛሬ ከእ​ና​ንተ ጋር ገና በሕ​ይ​ወት ሳለሁ እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐም​ፃ​ች​ኋል፤ ይል​ቁ​ንስ ከሞ​ትሁ በኋላ እን​ዴት ይሆ​ናል?


ለእ​ና​ንተ ከታ​ወ​ቀ​በት ቀን ጀምሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐመ​ፀ​ኞች ነበ​ራ​ችሁ።


“አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በም​ድረ በዳ ምን ያህል እን​ዳ​ሳ​ዘ​ን​ኸው፥ ከግ​ብፅ ሀገር ከወ​ጣ​ህ​በት ቀን ጀምሮ ወደ​ዚህ ስፍራ እስከ መጣ​ችሁ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ እን​ዳ​መ​ፃ​ችሁ አስብ፤ አት​ር​ሳም።


ሳኦ​ልም፦“ሕዝቡ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠ​ዉ​አ​ቸው ዘንድ ከበ​ጎ​ችና ከላ​ሞች መን​ጋ​ዎች መል​ካም መል​ካ​ሙን አድ​ነ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን አመ​ጣን፤ የቀ​ሩ​ት​ንም ፈጽሜ አጠ​ፋሁ” አለው።


ሕዝቡ ግን ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጌ​ል​ጌላ ይሠዉ ዘንድ ከእ​ርሙ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ከም​ር​ኮው ወሰዱ” አለው።


ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ሕዝ​ቡን ስለ ፈራሁ፥ ቃላ​ቸ​ው​ንም ስለ ሰማሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዝና የአ​ን​ተን ቃል በመ​ተ​ላ​ለፍ በድ​ያ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos