አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
ዘፍጥረት 44:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም አላቸው፥ “ይህን አደርግ ዘንድ አይገባኝም፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው እርሱ አገልጋይ ይሁነኝ እንጂ፤ እናንተ ግን ወደ አባታችሁ በደኅና ሂዱ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም፣ “ይህንስ ፈጽሞ አላደርገውም፤ ባሪያዬ የሚሆነው ጽዋው የተገኘበት ሰው ብቻ ነው፤ የቀራችሁት በሰላም ወደ አባታችሁ ተመለሱ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም፥ “ይህንንስ ፈጽሞ አላደርገውም፤ ባርያዬ የሚሆነው ጽዋው የተገኘበት ሰው ብቻ ነው፤ የቀራችሁት በሰላም ወደ አባታችሁ ተመለሱ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍም “ይህንንስ ከቶ አላደርገውም! ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ የእኔ ባሪያ መሆን አለበት፤ ሌሎቻችሁ በሰላም ወደ አባታችሁ መመለስ ትችላላችሁ!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም እላቸው፦ ይህን አደርግ ዘንድ አይሆንልኝም ጽዋው የተገኘበቱ ሰው እርሱ ባሪያ ይሁነኝ እናንተም ወደ አባታችሁ በደኅና ውጡ። |
አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
አምላክህ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር እንደ አለ በአየን ጊዜ በአንተና በእኛ መካከል መሐላ ይሁን፤ አንተ በእኛ ላይ ክፉ እንዳታደርግ፤ እኛም በአንተ ላይ ክፉ እንዳናደርግ እንማማላለን።”
እርሱም አለ፥ “አሁንም እንዲሁ እንደ ነገራችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ አገልጋይ ይሁነኝ፤ እናንተም ንጹሓን ትሆናላችሁ።”
ይሁዳም አለ፦ “ለጌታችን ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የአገልጋዮችህን ኀጢአት ገለጠ። እነሆ፥ እኛም ጽዋው ከእርሱ ዘንድ የተገኘበትም ደግሞ ለጌታችን አገልጋዮቹ ነን።”
ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እንዲህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ በፊትህ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ፤ እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ፤ አንተ ከፈርዖን ቀጥለህ ነህና።
የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ጠባቂ በምሳሌ እንዲህ አለኝ፦ “እግዚአብሔርን መፍራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰዎች መካከል ተናገርሁ፥”