ዘፍጥረት 43:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ እዋሳለሁ፤ ከእጄ ትሻዋለህ፤ ወደ አንተ ባላመጣው፥ በፊትህም ባላቆመው፥ በዘመናት ሁሉ አንተን የበደልሁህ ልሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኀላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘላለም በደለኛው እኔ ልሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኀላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘለዓለም በደለኛ እኔ ልሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጁን በእኔ ዋስትና ስጠኝ፤ ስለ እርሱ እኔ ተጠያቂ እሆናለሁ፤ በደኅና ወደ አንተ መልሼ ባላመጣው በሕይወቴ ዘመን ተወቃሽ ልሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ስለ እርሱ እዋሳለሁ ከእጄ ትሻዋለህ ወደ አንተ ባላመጣው በፊትህም ባላቆመው በዘመናት ሁሉ አንተን የበደልሁ ልሁን። |
ሮቤልም አባቱን አለው፥ “ወደ አንተ መልሼ ያላመጣሁት እንደሆነ ሁለቱን ልጆችን ግደል፤ ልጅህን በእጄ ስጠኝ፤ እኔም ወደ አንተ እመልሰዋለሁ።”
ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፤ ከሰውም እጅ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።
የቴቁሔዪቱም ሴት ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ኀጢአቱ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ንጹሕ ይሁን” አለችው።
እኔ ኀጢአተኛውን፥ “በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ አንተም ባትነግረው፥ ነፍሱም እንድትድን ከክፉ መንገዱ ይመለስ ዘንድ ለኀጢአተኛው ባትነግረው፥ ያ ኀጢአተኛ በኀጢአቱ ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኀጢአት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱ ዕንቅፋት ባደርግ፥ እርሱ ይሞታል፤ አንተም አልነገርኸውምና በኀጢአቱ ይሞታል፤ ያደረጋትም የጽድቅ ነገር አትታሰብለትም፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
ጕበኛው ግን ጦር ሲመጣ ቢያይ፥ መለከቱንም ባይነፋ፥ ሕዝቡንም ባያስጠነቅቅ፥ ጦርም መጥቶ አንድ ሰው ከእነርሱ ቢወስድ፥ እርሱ በኀጢአቱ ተወስዶአል፤ ደሙን ግን ከጕበኛው እጅ እፈልጋለሁ።
ኀጢአተኛውን፦ ኀጢአተኛ ሆይ! በርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኀጢአተኛውን ከክፉ መንገዱ ታስጠነቅቅ ዘንድ ባትናገር፥ ያ ኀጢአተኛ በኀጢአቱ ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።