እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፥ “በእውነት ወንድማችንን በድለናል፤ እኛን በመማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውምና፤ ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።”
ዘፍጥረት 43:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያም ሰዎች ወደ ዮሴፍ ቤት እንደ ገቡ በአዩ ጊዜ እንዲህ አሉ፥ “በዓይበታችን ቀድሞ ስለ ተመለሰው ብር ሊተነኰሉብን፥ ሊወድቁብንም፥ እኛንም በባርነት ሊገዙን፥ አህዮቻችንንም ሊወስዱ ወደዚህ አስገቡን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹም ወደ ዮሴፍ ቤት በመወሰዳቸው ፈሩ፤ እነርሱም፣ “ወደዚህ የመጣነው፣ ቀደም ሲል እዚህ መጥተን ስንመለስ በየስልቾቻችን ውስጥ ተመልሶ በተጨመረው ብር ሰበብ ነው። ሰውየው ጥቃት ሊፈጽምብን፣ አስገድዶ ባሮቹ ሊያደርገንና አህዮቻችንን ሊቀማን ይፈልጋል” ብለው ሠጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ወደ ዮሴፍ ቤት በመወሰዳቸው ፈሩ፤ እነርሱም፥ “ወደዚህ የመጣነው፥ ቀደም ሲል እዚህ መጥተን ስንመለስ በየስልቾቻችን ውስጥ ተመልሶ በተጨመረው ብር ሰበብ ነው። ሰውዬው ጥቃት ሊፈጽምብን፥ አስገድዶ ባሮቹ ሊያደርገንና አህዮቻችንን ሊቀማን ይፈልጋል” ብለው ሠጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወደ እዚህ ያመጡን በመጀመሪያ ጊዜ በስልቻዎቻችን ውስጥ ተመልሶ ስለ ተገኘው ገንዘብ ሳይሆን አይቀርም” በማለት፤ ሰዎቹ ወደ ዮሴፍ ቤት በሚሄዱበት ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ “በዚህ ምክንያት ያሠቃዩናል፤ አህዮቻችንን ወስደው እኛንም የእነርሱ ባሪያዎች ያደርጉናል” ብለውም አሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ወደ ዮሴፍ ቤት ስለ ገቡ ፈሩ እንዲህም አሉ፦ በዓይበታችን ቀድሞ ስለ ተመለሰው ብር ሊተነኮልብን ሊወድቅብንም እኛንም በባርነት ሊገዛ አህዮቻችንንም ሊወስድ ወደዚህ አስገባን። |
እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፥ “በእውነት ወንድማችንን በድለናል፤ እኛን በመማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውምና፤ ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።”
ከእነርሱም አንዱ በአደሩበት ስፍራ ለአህዮቹ ገፈራን ይሰጥ ዘንድ ዓይበቱን ፈታ፤ ብሩንም በዓይበቱ አፍ ተቋጥሮ አገኘ።
ለወንድሞቹም፥ “ብሬ ተመለሰችልኝ፤ እርስዋም በዓይበቴ አፍ እነኋት” አላቸው። ልባቸውም ደነገጠ፤ እየታወኩም እርስ በርሳቸው ተባባሉ፥ “እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ምንድን ነው?”
እንዲህም ሆነ፤ ዓይበታቸውን በፈቱ ጊዜ እነሆ፥ ከእነርሱ እያንዳንዳቸው ብራቸውን በዓይበታቸው ተቋጥሮ አገኙት፤ እነርሱም አባታቸውም የተቋጠረ ብራቸውን አይተው ፈሩ።
በየዓይበታችን አፍ ያገኘነውን ብር እንኳን ይዘን ከከነዓን ሀገር ወደ አንተ ተመልሰናል፤ ከጌታህስ ቤት ወርቅ ወይስ ብር እንዴት እንሰርቃለን?
ለዳዊት ቤትም፥ “አራም ከኤፍሬም ጋር ተባብረዋል” የሚል ወሬ ተነገረ፤ የእርሱም ልብ የሕዝቡም ልብ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ ተናወጠ።
ያችም ትእዛዝ ለኀጢአት ምክንያት ሆነቻት፤ ምኞትንም ሁሉ አመጣችብኝ፤ ቀድሞ ግን ኦሪት ሳትሠራ ኀጢአት ሙት ነበረች።
የነውር ነገርም ቢያመጣባት፥ እኔ ይህችን ሴት ሚስቴ አድርጌ አገባኋት፤ በደረስሁባትም ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁባትም ብሎ ክፉ ስም ቢያወጣባት፥
እነሆም፦ በልጅህ ድንግልና አላገኘሁባትም ብሎ የነውር ነገር አወራባት፤ የልጄም የድንግልናዋ ልብስ ይኸው ይላቸዋል። በከተማም ሽማግሌዎች ፊት ልብሱን ይዘረጋሉ።
አባቱና እናቱም ነገሩ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ አላወቁም፤ እርሱ ከፍልስጥኤማውያን በቀልን ይመልስ ዘንድ ይፈልግ ነበርና። በዚያም ወራት ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ይገዙ ነበር።