La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 43:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮሴ​ፍም ብን​ያ​ምን ከእ​ነ​ርሱ ጋር በአ​የው ጊዜ የቤ​ቱን አዛዥ እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “እነ​ዚ​ያን ሰዎች ወደ ቤት አስ​ገ​ባ​ቸው፤ እር​ድም እረድ፤ አዘ​ጋ​ጅም፤ እነ​ዚያ ሰዎች በእ​ኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበ​ላ​ሉና።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋራ ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፣ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፤ ዛሬ ቀትር ላይ ዐብረውኝ ስለሚበሉ ፍሪዳ ተጥሎ ምሳ ይዘጋጅ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፥ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፤ ዛሬ ቀትር ላይ አብረውኝ ስለሚበሉ ፍሪዳ ተጥሎ ምሳ ይዘጋጅ” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮሴፍ ብንያምን ከእነርሱ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ ጠራውና “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ውሰዳቸው፤ ዛሬ ቀን ከእኔ ጋር ምሳ ስለሚበሉ አንድ ከብት ዕረድና አዘጋጅ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮሴፍን ብንያምብ ከእነርሱ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ እነዚይን ሰዎች ወደ ቤት አስገባቸው እርስም እረድ አዘጋጅም፥ እነዚይ ሰዎች በእኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበላሉና።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 43:16
12 Referencias Cruzadas  

አብ​ራ​ምም፥ “አቤቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ምን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ? እነሆ፥ ልጅ ሳል​ወ​ልድ እሞ​ታ​ለሁ፤ የቤ​ቴም ወራሽ ከዘ​መዴ ወገን የሚ​ሆን የደ​ማ​ስቆ ሰው የማ​ሴቅ ልጅ ይህ ኢያ​ው​ብር ነው” አለ።


ሕፃ​ኑም አደገ፤ ጡት​ንም አስ​ጣ​ሉት፤ አብ​ር​ሃ​ምም ይስ​ሐ​ቅን ጡት ባስ​ጣ​ለ​በት ቀን ትልቅ ግብ​ዣን አደ​ረገ።


ይስ​ሐ​ቅም ማዕድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ በሉም፤ ጠጡም።


ያዕ​ቆ​ብም በተ​ራ​ራው ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ጠራ፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም በተ​ራ​ራው አደሩ።


ያም ሰው ዮሴፍ እን​ዳ​ለው አደ​ረገ፤ ሰዎ​ቹ​ንም ወደ ዮሴፍ ቤት አስ​ገባ።


ወደ ዮሴፍ ቤት አዛ​ዥም ቀረቡ፤ በቤ​ቱም ደጅ ተና​ገ​ሩት፤


ዮሴ​ፍም የቤ​ቱን አዛዥ እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “የእ​ነ​ዚህ ሰዎች ዓይ​በ​ቶ​ቻ​ቸው መያዝ የሚ​ች​ሉ​ትን ያህል እህል ሙላ​ላ​ቸው፤ የሁ​ሉ​ንም ብር በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ቸው አፍ ጨም​ረው፤


ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ወጥ​ተው ገና ሳይ​ርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እን​ዲህ አለ፥ “ተነ​ሥ​ተህ ሰዎ​ቹን ተከ​ት​ለህ ያዛ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ በመ​ል​ካሙ ፈንታ ስለ​ምን ክፉን መለ​ሳ​ችሁ?


ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋንም በማድጋዋ ጨመረች። ማዕድዋን አዘጋጀች።


እን​ጀ​ራ​ዬ​ንና የወ​ይን ጠጄን፥ ለሸ​ላ​ቾ​ቼም ያረ​ድ​ሁ​ትን ሥጋ ወስጄ ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ለማ​ላ​ው​ቃ​ቸው ሰዎች እሰ​ጣ​ለ​ሁን?”