እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራው” ተባባሉ።
ዘፍጥረት 42:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም፥ “ምናልባት ክፉ እንዳያገኘው” ብሎአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን፣ ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሀት ከወንድሞቹ ጋራ አልላከውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን፥ ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሀት ከወንድሞቹ ጋር አላከውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን “ጒዳት ይደርስበታል” ብሎ ስለ ፈራ ያዕቆብ ከዮሴፍ ጋር ከአንድ እናት የወለደውን ልጁን ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ወደ ግብጽ አላከውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍ ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም፦ ምናልባት ክፋ እንዳያግኘው ብሎአልና። |
እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራው” ተባባሉ።
እግዚአብሔር አምላክም አለ፥ “እነሆ፥ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘለዓለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፥”
እርሱም አለ፥ “ልጄ ከእናንተ ጋር አይወርድም፤ ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና፤ በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፉ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።”
አምላኬም በዚያ ሰው ፊት ሞገስን ይስጣችሁ፤ ያን ወንድማችሁንና ብንያምንም ይመልስላችሁ፤ እኔም ልጆችን እንዳጣሁ አጣሁ።”
ዮሴፍም ዐይኑን አንሥቶ የእናቱን ልጅ ወንድሙ ብንያምን አየው፤ እርሱም አለ፥ “ወደ አንተ እናመጣዋለን ብላችሁ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነውን?” እነርሱም፥ “አዎን” አሉት። እንዲህም አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ።”