ዘፍጥረት 42:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አለ፥ “እነሆ፥ እህል በግብፅ እንዳለ ሰምቼአለሁ፤ ወደዚያ ውረዱ፤ እንድንድንና በራብ እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጽ እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ከመሞት መሰንበት ይሻላልና ወደዚያው ወርዳችሁ እህል ሸምቱልን” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብጽ እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ከመሞት መሰንበት ይሻላልና ወደዚያው ወርዳችሁ እህል ሸምቱልን” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግብጽ አገር እህል መኖሩን ሰምቼአለሁ፤ በራብ እንዳንሞት ወደዚያ ሂዱና እህል ሸምቱልን” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም አለ፦ እነሆ ስንዴ በግብፅ እንዲገኝ ሰምቼአለሁ፤ ወደዚይ ውረዱ፥ እንድንድንና እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን። |
ከግብፅም ያመጡትን እህል በልተው ከፈጸሙ በኋላ አባታቸው፥ “እንደገና ሂዱ፤ ጥቂት እህል ሸምታችሁ አምጡልን” አላቸው።
ይሁዳም አባቱን እስራኤልን አለው፥ “እኛና አንተ ልጆቻችንም ደግሞ እንድንድን፥ እንዳንሞትም ብላቴናውን ከእኔ ጋር ላከው፤ እኛም ተነሥተን እንሄዳለን።
አሁንም ፈጥናችሁ ወደ አባቴ ሂዱ፤ እንዲህም በሉት፦ ልጅህ ዮሴፍ የሚለው ነገር ይህ ነው፦ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደረገኝ፤ ወደ እኔ ና፤ በዚያም አትዘግይ፤
በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ለሞት እስኪደርስ ታመመ። ነቢዩም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል” አለው።