ዘፍጥረት 41:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም የዮሴፍን ስም “እስፍንቶፎኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ የምትሆን አስኔትንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም ዮሴፍን ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱ ኦን ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ዮሴፍን “ጸፍናት ፐዕናህ” ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱጠ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈርዖን ለዮሴፍ “ጻፍናት ፐዕናሕ” የሚል መጠሪያ ስም አወጣለት፤ አስናት ተብላ የምትጠራውን የጶጢፌራን ልጅ በሚስትነት ሰጠው፤ ጶጢፌራ ኦን ተብሎ በሚጠራው ከተማ ካህን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም የዮሴፍን ስም ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ጠራው የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ የምትሆን አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በግብፅ ምድር ሁሉ ወጣ። |
ለዮሴፍም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ አስኔት የወለደችለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይመጣ ተወለዱለት።
ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ አስኔት የወለደችለት ምናሴና ኤፍሬም ናቸው። ሶርያዊት ዕቅብቱ የወለደችለት የምናሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ የምናሴም ወንድም የኤፍሬም ልጆች ሱታላና ጠኀን ናቸው። የሱታላ ልጅም ኤዴን ነው።
ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ይጠብቁ ነበር፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ሊያጠጡ የውኃዉን ገንዳ ሞሉ።
ከመካከላቸውም አጋቦስ የተባለ አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ጽኑ ረኃብ እንደሚመጣ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ተናገረ፤ ይህም በቄሣር ቀላውዴዎስ ዘመን ሆነ።