ዘፍጥረት 36:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ፤ ዔሳውም ኤዶም ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ፥ ዔሳው ኤዶም ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው በተራራማው አገር በኤዶም ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ ዔሳውም ኤዶም ነው። |
እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “ለጌታዬ ለዔሳው፦ ባሪያህ ያዕቆብ እንዲህ አለ ብላችሁ ንገሩት፦ በላባ ዘንድ በስደት ተቀመጥሁ፤ እስከ ዛሬ ድረስ ቈየሁ፤
መግዴኤል መስፍን፥ ኤራም መስፍን፤ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም መሳፍንት ናቸው። የኤዶማውያንም አባት ይህ ዔሳው ነው።
ከስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለቆቻቸውም የይሰዔ ልጆች ፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ።
አሁንም እነሆ፥ እስራኤል ከግብዕ ምድር በወጡ ጊዜ ያልፉባቸው ዘንድ ያልፈቀድህላቸው የአሞንና የሞዓብ ልጆች፥ የሴይርም ተራራ ሰዎች እንዳያጠፉአቸው ከእነርሱ ፈቀቅ ብለው ነበር።
የአሞንና የሞዓብ ልጆችም በሴይር ተራራ በሚኖሩት ላይ ፈጽመው ይገድሉአቸው ዘንድ፥ ያጠፉአቸውም ዘንድ ተነሥተውባቸው ነበር፤ በሴይርም የሚኖሩትን ካጠፉ በኋላ እርስ በርሳቸው ሊጠፋፉ ተነሡ።
በሞዓብና በአሞንም ልጆች መካከል፥ በኤዶምያስም፥ በምድርም ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ቅሬታ እንዳስቀረ፥ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው ሰሙ።
የአብድዩ ራእይ። ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከእግዚአብሔር ዘንድ መስማትን ሰማሁ፤ ከባቢን ወደ አሕዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላይዋም እንነሣና እንውጋት።
በተሰነጠቀም ዓለት ውስጥ እንደሚኖር- ማደሪያውንም ከፍ ከፍ እንደሚያደርግ፥ በልቡም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? እንደሚል፥ የልብህ ትዕቢት እጅግ አኵርቶሃል።
ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ እነርሱ ወረሱአቸው፤ በእነርሱም ፋንታ እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።
ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች ሀገር ታልፋላችሁ፤ እነርሱ ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ።
የሴይርን ተራራ ለዔሳው ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳን አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።
ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ የያዕቆብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረቱም፤ ግብፃውያንም መከራ አጸኑባቸው።
ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፤ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከቢዖርም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።