La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 36:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዔሳ​ውም ሚስ​ቶ​ቹን፥ ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንና ሴቶች ልጆ​ቹን፥ ቤተ ሰቡ​ንም ሁሉ፥ እን​ስ​ሶ​ቹ​ንም ሁሉ፥ በከ​ነ​ዓ​ንም ሀገር ያገ​ኘ​ውን ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ይዞ ከወ​ን​ድሙ ከያ​ዕ​ቆብ ፊት ከከ​ነ​ዓን ሀገር ሄደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዔሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዔሳውም ሚስቶቹን፥ ወንዶች ልጆቹንና ሴቶች ልጆቹን፥ ቤተሰቡንም ሁሉ፥ እንስሶቹንም ሁሉ፥ በከነዓንም ሀገር ያገኘውን ንብረቱን ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ ዔሳው ሚስቶቹን ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፥ በቤቱ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ መንጋዎቹንና ሌሎቹንም ከብቶች ሁሉ፥ በከነዓን ሳለ ያፈራውን ንብረት ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዔሳውም ሚስቶቹን ወንዶች ልጅቹንና ሴቶች ልጆቹን ቤተሰቡንም ሁሉ ከብቱንም ሁሉ እንስሶቹንም ሁሉ በከንዓንም አገር ያገኘውን ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ፊት ወደ ሌላ አገር ሄደ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 36:6
10 Referencias Cruzadas  

አብ​ራ​ምም ሚስ​ቱን ሦራ​ንና የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገ​ኙ​ትን ከብት ሁሉና በካ​ራን ያገ​ኙ​አ​ቸ​ውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነ​ዓን ምድር ለመ​ሄድ ወጣ፤ ወደ ከነ​ዓ​ንም ምድር ገቡ።


ሎጥም ለራሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ውን ሀገር ሁሉ መረጠ፤ ሎጥም ወደ ምሥ​ራቅ ተጓዘ፤ አን​ዱም ከሌ​ላው እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ።


በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይቀ​መጡ ዘንድ ምድር አል​በ​ቃ​ቸ​ውም፤ ንብ​ረ​ታ​ቸው ብዙ ነበ​ርና፤ ስለ​ዚ​ህም ባን​ድ​ነት ይቀ​መጡ ዘንድ ምድር አል​በ​ቃ​ቻ​ቸ​ውም።


በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ር​ባ​ትን ይህ​ችን ምድር፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ሁሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​አት ዘንድ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አላት፥ “ሁለት ሕዝ​ቦች በማ​ኅ​ፀ​ንሽ አሉ፤ ሁለ​ቱም ሕዝብ ከሆ​ድሽ ይወ​ለ​ዳሉ፤ ሕዝ​ብም ከሕ​ዝብ ይበ​ረ​ታል፤ ታላ​ቁም ለታ​ናሹ ይገ​ዛል።”


ስደ​ተኛ ሆነህ የተ​ቀ​መ​ጥ​ህ​ባ​ትን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የሰ​ጣ​ትን ምድር ትወ​ርስ ዘንድ የአ​ባ​ቴን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን በረ​ከት ለአ​ንተ ይስ​ጥህ፤ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ።”


ያዕ​ቆ​ብም ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም ሀገር በፊቱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤


ኤሌ​ባ​ማም ዮሔ​ልን፥ ይጉ​ሜ​ልን፥ ቆሬ​ንም ወለ​ደች። በከ​ነ​ዓን ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የዔ​ሳው ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


ያዋ​ንና ቶቤል፥ ሞሳ​ሕም ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ንግ​ድ​ሽ​ንም በሰ​ዎች ነፍ​ሳ​ትና በናስ ዕቃ አደ​ረጉ።


ቀረፋም፥ ቅመምም፥ የሚቃጠልም ሽቱ፥ ቅባትም፥ ዕጣንም፥ የወይን ጠጅም፥ ዘይትም፥ የተሰለቀ ዱቄትም፥ ስንዴም፥ ከብትም፥ በግም፥ ፈረስም፥ ሰረገላም፥ ባሪያዎችም፥ የሰዎችም ነፍሳት ነው።