ዘፍጥረት 36:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመንገሡ በፊት በኤዶም ሀገር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእስራኤል ምንም ንጉሥ ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእስራኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመኖሩ በፊት በኤዶም አገር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእስራኤል ንጉሥ መንገሥ ከመጀመሩ በፊት በኤዶም ምድር የነገሡት ነገሥታት የሚከተሉት ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመኖሩ በፊት በኤዶም አገር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። |
እግዚአብሔርም አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይወለዳሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
እግዚአብሔርም አለው፥ “አምላክህ እኔ ነኝ፤ ብዛ፤ ተባዛም፤ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፤ ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ።
ዲሶን መስፍን፥ ኤሶር መስፍን፥ ሪሶን መስፍን፤ በሴይር ምድር በየሹመታቸው መሳፍንት የሆኑ የሖሪ መሳፍንት እነዚህ ናቸው።
ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፥ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤
እስራኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማንነው? እርሱ ያጸንሃል፤ ይረዳሃልም፤ ትምክሕትህ በሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ ውሸታሞች ናቸው፤ አንተም በአንገታቸው ላይ ትጫናለህ።”