ያዕቆብም ወንድሞቹን፥ “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው፤ እነርሱም ድንጋይ ሰብስበው ከመሩ፤ በድንጋዩም ክምር ላይ በሉ።
ዘፍጥረት 31:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አቆመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አቆመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ያዕቆብ ትልቅ ድንጋይ አንሥቶ የመታሰቢያ ሐውልት እንዲሆን አቆመው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አቆመ። |
ያዕቆብም ወንድሞቹን፥ “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው፤ እነርሱም ድንጋይ ሰብስበው ከመሩ፤ በድንጋዩም ክምር ላይ በሉ።
ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ሐውልት ተከለ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፤ ዘይትንም አፈሰሰበት።
ኢያሱም ይህን ቃል ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ጻፈው፤ ኢያሱም ታላቁን ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር ፊት በነበረችው በአሆማ ዛፍ በታች አቆማት።
ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ፥ “ይህች ድንጋይ በእናንተ ላይ ምስክር ናት፤ እርስዋ፥ ዛሬ እንደ ነገራችሁ በእግዚአብሔር ዘንድ የተባለውን ሁሉ ሰምታለችና በኋላ ዘመን አምላኬን እግዚአብሔርን ብትክዱት ይህች ድንጋይ ምስክር ትሆንባችኋለች” አላቸው።