Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 24:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ኢያ​ሱም ይህን ቃል ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መጽ​ሐፍ ጻፈው፤ ኢያ​ሱም ታላ​ቁን ድን​ጋይ ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በነ​በ​ረ​ችው በአ​ሆማ ዛፍ በታች አቆ​ማት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ኢያሱም እነዚህን ቃሎች እግዚአብሔር የሕግ መጽሐፍ ጻፋቸው፤ ትልቅ ድንጋይም ወስዶ በባሉጥ ዛፍ ሥር፣ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ስፍራ አጠገብ አቆመው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ኢያሱም እነዚህን ቃላት በጌታ ሕግ መጽሐፍ ጻፈ፤ ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በጌታ መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ኢያሱም እነዚህን ትእዛዞች በእግዚአብሔር የሕግ መጽሐፍ ጻፈ፤ ከዚያም በኋላ አንድ ትልቅ ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ በሚገኘው የወርካ ዛፍ ሥር አቆመው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ኢያሱም ይህን ቃል ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ጻፈ፥ ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 24:26
10 Referencias Cruzadas  

የሰ​ቂ​ማም ሰዎች ሁሉ፥ የመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት ሁሉ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሄደ​ውም በሰ​ቂማ በዐ​ምዱ አጠ​ገብ ባለው የወ​ይራ ዛፍ በታች አቤ​ሜ​ሌ​ክን አነ​ገሡ።


በእ​ጃ​ቸው ያሉ​ት​ንም እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክት ሁሉ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም ያሉ​ትን ጉት​ቾች ለያ​ዕ​ቆብ ሰጡት፤ ያዕ​ቆ​ብም በሴ​ቄም አጠ​ገብ ካለ​ችው ዛፍ በታች ቀበ​ራ​ቸው። እስከ ዛሬም ድረስ አጠ​ፋ​ቸው።


ሙሴም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለ​ዳም ተነሣ፤ ከተ​ራ​ራ​ውም በታች መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለ​ትም ድን​ጋ​ዮ​ችን ለዐ​ሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ አቆመ።


የር​ብቃ ሞግ​ዚት ዲቦ​ራም ሞተች፤ ከቤ​ቴል በታች ባላን በሚ​ባል ዛፍ ሥርም ተቀ​በ​ረች፤ ያዕ​ቆ​ብም ስሙን “የል​ቅሶ ዛፍ” ብሎ ጠራው።


ያዕ​ቆ​ብም ድን​ጋይ ወስዶ ሐው​ልት አቆመ።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios