እግዚአብሔርም አዳምን አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ከአዘዝሁህ ከዚያ ዛፍም በልተሃልና ምድር በሥራህ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤
ዘፍጥረት 3:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድርም እሾኽና አሜከላ ታበቅልብሃለች፤ ከቡቃያዋም ትበላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፥ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር እሾኽና አሜከላ ታበቅላለች፤ አንተም የዱር ተክሎችን ትበላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። |
እግዚአብሔርም አዳምን አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ከአዘዝሁህ ከዚያ ዛፍም በልተሃልና ምድር በሥራህ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤
ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራህን ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህና።”
እንዲህም አለ፥ “ከእናቴ ማኅፀን ራቁቴን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደ ምድር እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእግዚአብብሔር ስም የተባረከ ይሁን።”
ወደ ሰማይ የወጣ፥ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በብብቱ የሰበሰበ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርንስ ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው?
ባድማ አደርገዋለሁ፤ አይገረዝም፤ አይኰተኰትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፤ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ደመናዎችን አዝዛለሁ።
በዚያም ወራት እንዲህ ይሆናል፤ ወይን በሀገሩ ሁሉ የበጀ ይሆናል፤ የአንድ ሺህ የወይን ዳስ ዋጋ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ይሆናል። ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ እሾህንና ኵርንችትንም ትሞላለች፤ ፍርሀትም ይመጣል።
ስንዴን ትዘራላችሁ፤ እሾህንም ታጭዳላችሁ፤ ዕጣችሁም ምንም አይጠቅማችሁም፤ ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ በአዝመራችሁ ታፍራላችሁ።
እግዚአብሔር ለይሁዳ ወንዶችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲህ ይላልና፦ ልባችሁን አድሱ በእሾህም ላይ አትዝሩ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ መውደቂያና ወጥመድ፥ በእግራችሁም ችንካር፥ በዐይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል እንጂ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእንግዲህ ወዲያ እነዚህን አሕዛብ ከፊታችሁ እንዳያጠፋቸው ራሳችሁ ዕወቁ።