ልያም መውለድን እንዳቆመች በአየች ጊዜ አገልጋይዋን ዘለፋን ወሰደች፤ ሚስት ትሆነውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው፤ ያዕቆብም ወደ እርስዋ ገባ።
ዘፍጥረት 29:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ በዚህም ጊዜ “እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገና ፀንሳ አሁንም ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሷም፣ “እንግዲህ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስሙንም ይሁዳ ብላ ጠራችው። ከዚያም በኋላ መውለድ አቆመች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ፀነስች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች፥ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገና ፀነሰችና ወንድ ልጅ ወለደች፤ “አሁንስ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” ስትል ስሙን ይሁዳ አለችው፤ ከዚህ በኋላ መውለድ አቋረጠች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ፀነስች ወንድ ልጅንም ወለደች በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች። |
ልያም መውለድን እንዳቆመች በአየች ጊዜ አገልጋይዋን ዘለፋን ወሰደች፤ ሚስት ትሆነውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው፤ ያዕቆብም ወደ እርስዋ ገባ።
የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆችም፤ ጋድ፥ አሴር፤ እነዚህ በሁለቱ ወንዞች መካከል በሶርያ የተወለዱለት የያዕቆብ ልጆች ናቸው።
የይሁዳም ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስም ልጆች እኒህ ናቸው፤ ኤስሮም፥ ይሞሔል፤
የይሳኮር ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥
የይሁዳም በረከት ይህች ናት፤ አቤቱ የይሁዳን ቃል ስማ፤ ወደ ሕዝቡም ይግባ፤ እጆቹም ይግዙ፤ በጠላቶቹ ላይ ረዳት ትሆነዋለህ።